Saturday, November 4, 2017

መደማመጥ ቢኖር ኖሮ ፦፦

https://www.youtube.com/watch?v=kb0nAeufC3o
መከባበር ላይ የተመሰረተው የመኖር ዜይቤያችን መሰረቱን ለመናድ ተወጥኖ በተደራጀ መንግስታዊ ፖልሲ አንድንማር አንድናድግ ስንደረግ መርጠን ሳይሆን ተገደን ነበር ። ይህንን ፈር  ያጣ አፍራሽነት ማስተዋል የቻሉ የገዥዎች እጀ ሰፊነት ሳያስፈራቸው መከባበራችንን አንድነታችንን መልሱልን በቃችሁ ማለት መቻላቸውን ከእለት ወደ እለት በሀገሬ ማየት መቻሌ ነገሮችን ሰከን ብዬ ማስተዋል እና የተውለድኩበትን የተማርኩበትን ስርአተትምህርት አና ስርአት ከማማረር ይልቅ ፍትሕ  መከባበር እና በሁሉ የሁሉ የሆነ ስርአት መስራት እችላለሁ የምል እንድሆን አድርጎኛል ። 

በእርግጥ መከባበራችንን የሚያስተምሩን ለእኔ እና አንተ የሆነችውን ሀገር ለመስራት አለኝ የሚሉት ሃብት ንብረት እንዲሁም ህይወታቸውን እየገበሩ ያሉ ወገኖች ወገን ስማ ብለው ሲጮሁ ያለመስማታችን ፈተናችንን አበዛብን ። 
በተለይ ወጣቱ ትውልድ የኔ የምትለውን እየቀሙህ ያሉት ጠባቦች አንተን መስለው ሲገሉህ የማይሽንጥህ ምን ሆነህ ነው ??? 
 ወገን መደማመጥ ቢኖር የፈረሱን ምግብ ለውሻ ባልሰጠነው ። ሀገር ይኑረን ከፋፋዮችን በቃቹ እንበላቸው!!


ፍቅሬ ነኝ  

ሕልም አለኝ ከአርበኛ ታጋይ ዕዝራ ዘለቀ ከኤርትራ


November 1, 2017 
ሕወሃት/ኢሕአዴግ መሰረቱ ተናግቶ እየተንገዳገደ ነው። መውደቁ እንዴትና መቼ የሚለው ጥያቄ ሊያነጋግር ይችላል። ግን መዉደቁ አይቀሬ ነው። ከብዙ ምልክቶቹ አንደኛውና ዋነኛው በአሁን ሰዓት በቄሮዎቹ የገጠመው የከረረና የመረረ ተቃውሞ ነው።
ሆኖም ግን ይህንን በእጅጉ አንገብጋቢ የሆነውንና ተገቢ ምላሽ የሚያስፈልገውን ሕዝባዊ ጥያቄ እንደተለመደው ችላ ብሎ ማለፍ ሕወሃትንም ሆነ አገራችንን ከፍተኛ ዋጋ እንደሚያስከፍል ሊታወቅ ይገባል። የነጻነትና የእኩልነት ብርሀን በምድረ ኢትዮጲያ እስከምትፈነጥቅ ድረስም ህዝባችንን እያንዘፈዘፈው ያለው የባርነት ክረምትና ለዚህም ስቃይ እየከፈለ ያለው ሕጋዊ ተቃውሞ መቀጠሉ የማይቀር ነው።በ2008 የታዩት የኦሮሚያና የአማራ ክልል ህዝባዊ ቁጣዎችም ሆኑ የወቅቱ የቄሮዎቹ እምቢተኝነት የመጪውንና የማይቀረውን ሱናሜ የሚያመላክቱ የማስጠንቀቂያ ደወሎች እንጂ የመጨረሻዎቹ እንዳልሆኑ መረዳት ያሻል ። የወጣት ዜጏቻችን ያደባባይ ተቃውሞዎችን ምንም አዲስ ነገር የሌለው፣ የተለመደ ጩኸት ብሎ ማናናቅና “የትም አይደርሱም ለጊዜው የተሰማቸውን ውጥረት ማስተንፈሻ ይሆናል” በሚል እሳቤ ወይንም በለመዱት የማወናበድ ስልት አንዱን ሽረው ሌላውን በማንገስ ሀገሪቱን ለማስተዳደር የሚሞክሩ የህወሃት ባለስልጣናት ካሸለቡበት እንቅልፍ የሚቀሰቀሱበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም። የእያንዳንዱ ሰው  መሰረታዊ የዜግነት መብቱ እስካልተጠበቀ ድረስ  ኢትዮጲያ ውስጥ ሰላምና ዕረፍት የሚባል ነገር ሊኖር አይችልም። መራራው ትግላችን በጣፋጭ ነጻነት እስከሚተካ ድረስ እንቅልፍ አይኖረንም።
እዚህ ላይ ለትግል ጓዶቼ የማስተላልፈው አንድ መልዕክት አለኝ። ወደፍትህ አለም በምናደርገው አድካሚና መራራ ጉዞ ውስጥ ማናቸውም አይነት የትግል ስልቶች ከጥላቻና ከበቀል የነጹ እንዲሆኑ አደራ እላችኋለሁ። ከሕወሃት/ኢሕአዴግ የአውሬና የጨለምተኝነት ባህሪ በተቃራኒው ቆመን ትግላችን ስለፍቅር፣ ስለ አንድነትና ስለ ሰላም መሆኑን ላፍታም ቢሆን መዘንጋት የለብንም።በጠቅላላው የሃገራችን ክፍል በተለይም ደግሞ በታሪካዊው የቄሮና የአማራ ወጣቶች የተቀጣጠለው የህዝባዊ ተቃውሞ መንፈስ የትግራይ ብሄር ተወላጅ የሆኑ ኢትዮጲያዊያንን በሙሉ በወያኔነት ፈርጀን በጥርጣሬና በስጋት እንዳናያቸው አደራ እላለሁ። የትግራይ ህዝብ ዝምታ ከስርዓቱ ጋር የመስማማትና የመሞዳሞድ ምክልት ነው ብለው ለሚያስቡ ሁሉ እንዲህ በሏቸው፡ “የትግራይ ህዝብ የታፈነና እንደሌሎች ወገኖቹ ሁሉ ነጻነትን የሚናፍቅ ነው። ኢትዮጲያ ያለትግራይ ትግራይም ያለ ኢትዮጲያ የሚታሰቡ አይደሉምና። ትግራይ የኢትዮጲያ ስልጣኔ መሰረት ናት። ዕጣ ፈንታችን ተሳስሯል። ሕወሃት እንጂ የሚፈርሰው ኢትዮጲያ አትፈርስም። የኛ አንድነት፣ የኛ ሕብረት፣ የኛ ኢትዮጲያዊነት በሕወሃት መቃብር ላይ ዳግም ያብባል”። በሏቸው።
ከእንግዲህ ትግላችን ወደፊትና ወደፊት ብቻ እንደሆነ ለራሳችን ቃል እንግባ! ወደኋላ አንመለስም! አንዳንድ የትግላችን መጨረሻ፣ የጉዞአችን መዳረሻ የነጻነት አደባባይ ብቻ መሆኑ ያልገባቸው ወይንም ሆን ብለው ትግላችንን ለማዘናጋት የተደራጁ የወያኔ ቅጥረኞች አሁንም ድረስ የስርዓቱን የሃሰት ፕሮፓጋንዳ እየጠቀሱ ጥያቄዎችን ያቀርቡልናል። “ኢሕአዴግ ልማት አምጥቷል፣ ድህነትን ቀንሷል፣ ዲሞክራሲዉንም ቢሆን በሂደት ያሳካልናል። ታዲያ እናንተ ምንድነው የምትፈልጉት? ምን ቢያደርግላችሁ ነው እርካታን የምታገኙት?”  ሲሉ ይጠይቁናል። የኛ መልስ አጭር፣ ግልጽና ቀጥተኛ ነው! ሕወሃት እስከ አፍንጫቸው ያስታጠቃቸው የአጋዚና የልዩ ሀይል ፖሊሶች ንጹሃን ዜጎቻችንን፣ እናቶቻችንን፣ አባቶቻችንን፣ እህቶቻችንን፣ ወንድሞቻችንንና ልጆቻችንን ባደባባይ እንደውሻ መግደል እስካላቆሙ ድረስ እርካታ አይኖረንም! እንደ ኢትዮጲያዊነታችን በመረጥነውና በፈቀድነው ቦታ የመኖር፣ የመስራት፣ ንግድ የማንቀሳቀስ፣ ንብረትና ቤተሰብ የማፍራት መብታችን እስካልተከበረ ድረስ እርካታ የሚባል ነገር አይኖረንም! በየሄድንበት ቦታ፣ በየተቀጠርንበት መስሪያ ቤት፣ በምንማርበት ትምህርት ቤት፣ በምንዳኝባቸው ፍርድቤቶችና ሌሎች ተቋማት ውስጥ የገዢው ብሄር አባላት ባለመሆናችን ወይንም ከስርዓቱ ጋር በአድርባይነት አስመስለን ለመኖር ባለመፍቀዳችን ብቻ የሚደርስብን አድልዖና መገፋት እስካላበቃ ድረስ እርካታ አይኖረንም! የኢትዮጲያ የወደፊት ተስፋ የሆኑ ወጣቶቻችን በነጻነትና በስራ እጦት ወደ ሌላ አለም ሲሰደዱ መንገድ ላይ ሆዳቸው እየተቀረደደ ኩላሊታቸው ለሽያጭ መቅረቡ እስካላቆመ ድረስ፣ አንገታቸው የአይሲስ ቢላዋ ሰለባ ወይንም የባሕር አውሬ ሲሳይ መሆኑ እስካላቆመ ድረስ ዕረፍት የለንም! ሴቶች ልጆቻችን ለአቅመ ሄዋን ሳይደርሱ በችግርና በችጋር መንገድ ላይ ቆመው ለሴተኛ አዳሪነት መጋለጣቸው እስካላቆመ ድረስ ዕርካታ አይኖረንም! የመከላከያ፣ የደህንነትና መሰል ተቋማት  የቀድሞውን የህብረ ብሄር ቅርጻቸውን ተመልሰው ይዘው ኢትዮጲያ ኢትዮጲያ እስካልሸተቱ ድረስ መቼም እርካታ አይኖረንም!  የዕብሪተኞቹ፣ የመሃይሞቹና የጠባቦቹ የነክቡር ፕሮፌሰር ጄኔራል ሳሞራ ዩኑስና ቢጤዎቹ የጡንቻ ዘመን ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እስካላበቃ ድረስ ዕረፍት አይኖረንም! ሕዝባችን ዲሞክራሲና ነጻ ምርጫ ስለሚባሉት ሃሳቦች ያለው ግንዛቤ ከምርጫ 97 ወዲህ ጤናማ አይደለም። ነጻ ምርጫን የሕወሃት/ አጋዚ አልሞ ተኳሾች ከሚያስከፍሉት የሕይወት ዋጋ ጋር ፈጽሞ መለየት የማይችልበት አሳዛኝና አስፈሪ ደረጃ ላይ ደርሷል። በመሆኑም እኛ የአርበኞች ግንቦት 7 አመራሮችና ስራዊት አባላት እያንዳንዱ ኢትዮጲያዊ በዲሞክራሲ ምርጫ ብቻ የሚፈልገውን መሪና ስርዓት መምረጥ እስካልቻለ ድረስ ዕርካታ የሚባል ነገር አይኖረንም! ለዚህ የሚከፈለውንም ከፍተኛ የህይወት ዋጋ ለመክፈል ከምንግዜውም በላይ ዝግጁነታችንን ስነግራችሁ የናንተን የማይናወጥ ድጋፍና ቁርጠኝነት ከግንዛቤ ውስጥ በመክተት ነው። ለዚህም የሚሰማኝ  ኩራትና ደስታ ወሰን የለውም!ባጭሩ እኛ ዕርካታን የምናገኘው የሕወሃት/ኢሕአዴግ አገዛዝ ወይ ወዶ ወይ ተገድዶ ለድርድር ባንድ ጠረጴዛ ሲቀመጥና የህዝባችንን የዕውነተኛ ዲሞክራሲ፣ የአንድነትና የሰላም ጥማቱን ለማርካት ሲዘጋጅ አሊያም ይህንን ሰውበላ አረመኔ ስርዓት ከስር መሰረቱ ገርስሰን ጥለን በመቃብሩ ላይ ዲሞክራሲን ስናውጅ ብቻና ብቻ ነው እርካታን የምናገኘው!
ዉድ ወገኖች!
ዛሬ ላይ የወያኔ/ሕወሃት ለ25 ዓመታት በላያችን ላይ ያሳደረብንን የፍርሃትና የምንቸገረኝነት ድባብ ሰብረን የወጣን እንደሆነ ይሰማኛል። በውጭ ዓለም የምትገኙ ኢትዮጲያዎያን ከዚህ የግፈኛ ስርዓት በብዙ ሺህ ማይልስ ርቃችሁና የወያኔ/ህወሃት ማስፈራራትና ዛቻ የማያገኛችሁ ቦታም ሆናችሁ ስለራሳችሁ ደህንነትና ሰላም መሆን ብቻ ሳታስቡ የቀረውን፣ ከኋላ ትታችሁት የመጣችሁትን፣ በገዛ አገሩ በባርነት ቀንበር የሚሰቃየውን ወገናችሁን ሳትረሱ አሁንም ለህዝባችሁ ነጻነት የምታደርጉትን ትግል ከፍተኛ ዋጋ የምንሰጠው ነው። እንድትቀጥሉበትም አደራ እላለሁ።እኛ ኢትዮጲያዊያንን ከሌሎች የዳያስፖራ ማሕበረሰቦች ልዩ የሚያደርገንም ይህ አለም የመሰከረልን ለኢትዮጲያ አገራችንና ለሕዝባችን ያለን ልዩ ፍቅር ነው። ከሀገራችን ርቀን በተለያዩ ዓለማት ብንሰደድም ሳትበላ ያበላችንን፣ ታርዛ ያለበሰችንን፣ ቆስላ ያከመችንን፣ አልቅሳ ዕምባችንን ያበሰችልንን እናታችንን ኢትዮጲያን አለመርሳታችን ነው።
ወድ ወገኖቼ! እያንዳንዱ ትውልድ ማለፍ ያለበት የራሱ የሆነ ልዩ ፈተና እንደሚገጥመው ታሪክ ያስተምረናል። የኛም ትውልድ የህወሃትን ስርዓት መታገል፣ መጣልና ዕዉነተኛ ዲሞክራሲን የማስፈን ሃላፊነት ተጥሎበታል። ስለሆነም የተስፋ መቁረጥ ምርጫ ከእንግዲህ የለንም። የዛሬው ጨለማ የነገውን ብርሃናችንን በፍጹም እንዳይጋርድብን አደራ እላለሁ።

ይህ አሁን የተያያዝነው የመጨረሻው የሞት ሽረት ትግል እሾህና አሜኬላ የበዛበት፣ የሕጻናትንና የአዛውንትን፣ የወጣቶቻችንንና የእናቶቻችንን ደም እያስገበረን ያለ የሰው ልጅን ትዕግስት በእጅጉ የሚፈትን ትግል ቢሆንም ፣ አሁንም ድረስ ግን ሕልም አለኝ! አዎን ሕልም አለኝ!
ያለፉት 25 ዓመተ ፍዳዎች ተገባድደው ደጋፊና ተቃዋሚ፣ ልማታዊና ጸረ-ልማት፣ ሰላም አክባሪና አሸባሪ፣ ታማኝና ተላላኪ፣ ጠባብና  ትምክህተኛ፣ ወርቅና መዳብ እየተባባልን ወገን ለይተን የተኳረፍንና ልብ ለልብ የተራራቅን ወንድምና እህትማማቾች በቅርብ ጊዜ ውስጥ በዲሞክራሲ ሸምጋይነት ታርቀን ዳግም ፍቅራችንን እንደምናድስ ሕልም አለኝ!
አዎን ሕልም አለኝ! ዳግም በአዲስ መንፈስ፣ ዳግም በአዲስ ዓይን እየተያየን ሁላችንም ካንድ ማሕጸን የወጣን ያንድ እናት ልጆች እንጂ አንዱ ልጅ ሌላው የእንጀራ ልጅ እንዳልሆንን የምናረጋግጥበት፣ ሁላችንም ኢትዮጲያዊያን፣ ሁላችንም የእናት ሀገራችን ጉዳይ የሚያገባን፣ የሃሳብ ልዩነቶቻችን በጠላትነት የሚያፈራርጁን ሳይሆን ይልቁንም ለዕውነተኛ ልማትና ዕድገት ወሳኝ መሳሪያ መሆኑን የምንገነዘብበት ቀን ሩቅ እንደማይሆን ሕልም አለኝ!
ሕጻናት ልጆቻችን አዲስ በምንመሰርታት ኢትዮጲያ ውስጥ የሚኖራቸው ቦታ የሚወሰነው በመጡበት ብሄር፣ በሚናገሩት ቋንቋ፣ በሚከተሉት ሃይማኖት ወይንም ምን ያህል ለስርዓቱ ባላቸው አድርባይነትና አጎብዳጅነት ሳይሆን እንደ አንድ ኢትዮጲያዊ ዜጋ በራሳቸው ማንነትና ምንነት ብቻ እንደሚሆን ሕልም አለኝ!
አዎን ወገኖቼ ሕልም አለኝ!
የእናቶቻችን አይን ለቅሶና ዋይታ ሀዘንና እሪታ በዝቶበት ደም መስሎ ቀልቷል። አዎን ለ25 የስቃይ፣ የመከራ፣ የውርደትና የሞት ዓመታት የልጆቻቸውንና የባሎቻቸውን አስከሬን ከየመንገዱ እየለቀሙ የቀበሩ እናቶቻችን አይኖቻቸው በዕምባ ብዛት ደክሟል። በሰው በላው የደርግ ዘመን አስከሬን ለመቀበል ልጅሽ የተገደለበትን የጥይት ዋጋ ክፈይ የተባለች እናት ዛሬ ደግሞ የልጅሽ አስከሬን ላይ እንደበርጩማ ተቀመጪበት ተብላ ትዋረዳለች፣ ትሰቃያለች። ሆኖም ግን እነኚህ የታደሉት ናቸው ማለት ይቻላል። በሕወሃት በማይታወቁ የጨለማ እስር ቤቶች ውስጥ፣ በሌሊት ተወስደው በየበረሃው በተቆፈሩ ጉድጓዶችና በየጥሻው ተጥለው ደብዛቸው ጠፍቶ የቀሩና የአውሬ ሲሳይ ሆነው ለቀሩት ልጆቻቸው ዕርማቸውን ሳያወጡ ቀንና ሌሊት ሲሳቀቁ የሚኖሩትን እናቶች ቤቱ ይቁጠራቸው። እኔ ግን ይህ የጨለማና የሰቀቀን ሕይወት ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እንደሚያቆምና የእናቶቻችን አይን የሰላም፣ የደስታና የተስፋ ብርሃን እንደሚያፈነጥቅ ሕልም አለኝ!
ሌላም ሕልም አለኝ! በህወሃት ዘመን የሰውን ልጅ የማዋረጃ፣ የማሰቃያና የመግደያ ማዕከል የነበሩት የቂሊንጦ፣ የዝዋይ፣ የቃሊቲና የማዕከላዊ እስር ቤቶች ከእንግዲህ ወዲህ እንደ ጀርመን ናዚዎቹ አውሽቪትዝና ዛክሰንሃውስ ስለአምባገነኖች የመጨረሻው አስጸያፊ መገለጫነት የሚያስተምሩ የጥፋት ተቋማት መገለጫነት ሆነው የሚያስተምሩ ሙዚየሞችና ለታሪክ ባለሙያዎችም መመራመሪያ ብቻ ሆነው የሚያገለግሉ ማዕከላት እንጂ ማንም ዜጋ የተለየ ሃሳብ ስላለው ወይንም ስላላት ስብዕናቸው የሚገፈፍበት፣ የሚሰደቡበት፣ የሚዋረዱበት፣ ገላቸው የሚተለተልበትና ሬሳቸው እንደ ውሻ እየተጎተተ የማይጣልበት እንደሚሆኑ ሕልም አለኝ!
ባለፈው ጊዜ አንድ የትግራይ ወጣት “እኔ ትግሬ በመሆኔ ብቻ ከሌሎች ኢትዮጲያዊያን ጋር ስለሀገሬ ጉዳይ በነጻነት ማውራት አልቻልኩም። ምክንያቱም ትግራይነቴ  የሕወሃት ደጋፊ አድርጎ ስለሚያስጠረጥረኝ” ያለውን አስታውሳለሁ። እኔ ግን ያ የትግራይ ወጣትና እሱን ጠርጥረው ያገሸሹት ወንድምና እህቶቹ በቅርብ ጊዜ በነጻነት ማንም ማንንም ሳይፈራ፣ ሳይጠረጥር በእኩል ያገር ልጅነት መንፈስ እንደ ዜጋ ስለ አንዲት እናት ሀገራቸው ልብ ለልብ እንደሚወያዩ፣ እንደሚከራከሩና መፍትሄም በጋራ እንደሚያመነጩ ጠንካራ ዕምነቴ ነው። ይህ ሊሆን ግን ሌላው ኢትዮጲያዊ እንደሚያደርገው ሁሉ የትግራይ ልሂቃንና ወጣቶች፣ያገር ሽማግሌዎችና የሃይማኖት መሪዎች ድምጻችሁን ከፍ አድርጋችሁ ሕወሃትን በቃህ ልትሉት ግድ ነው። ጊዜው አሁን ነው። ሕወሃትን በጥገናዊ ለውጥ እናሻሽለዋለን፣ እናድሰዋለን፣ ዳግመኛ አፈር አስልሰን እናስነሳዋለን የምትሉ ተስፈኞች አንድም ከጥቅም፣ አንድም ከጠባብ ዘረኝነት አሊያም ደግሞ ከፍጹም የዋህነት የመነጨ አስተሳሰብ ነውና ዳግም ውስጣችሁን ፈትሹ! የሚታደስ፣ የሚሻሻል፣ የሚለወጥ ሕይወት ያለው፣ ተስፋ ያለው ነገር ነው። ሕወሃት በስብሷል፣ ሕወሃት ሞቷል። በሙት መንፈስ የሚንቀሳቀስ የዞምቢዎች ስብስብ ነው የዛሬው ሕወሃት ማለት!
ወድ የትግራይ ተወላጅ የሆናችሁ ኢትዮጲያዊያን ወገኖች! ቀዳማይ ወያኔዎች ከባሌና ከጎጃም አርሶ አደር ወንድሞቻቸው ጋር ዕምቢ ለንጉሱ፣ ዕምቢ ለባርነት ብለው ያመጹትና መከራን የተቀበሉት ከሌሎች ወገኖቻቸው ጋር አብረው በጋራ የተሸከሙትን የባርነት ቀንበር አብረው ጥለው የኢትዮጲያን ትንሳኤ ባንድነት ሊያውጁ እንጂ የነሱን አቅልለው ጥለው የሌላውን ወገናቸውን የስቃይና የባርነት ቀንበር ለማጠጠር አልነበረም። በነኚህ ጀግኖች አባቶቻችሁና አያቶቻችሁ ስም የሚፈጸመውን ወንጀል ባደባባይ መኮነን ይኖርባችኋል። በተለያዩ የኢትዮጲያ አካባቢዎች በናንተ በትግሬዎች ስም የሚፈጸሙት ወንጀሎች ጠንብተውና ከርፍተው እንኳንስ ምድሪቷን ሰማዩንም እያገሙት ነው። የሕዝቡ ለቅሶና ጸሎት የማታ ማታ የእግዚአብሄር ጆሮ ገብቷል። አያቶቻችሁ ዕምቢ ለንጉሱ ዕምቢ ለባርነት እንዳሉት ሁሉ እናንተም ዕምቢ ለሕወሃት ዕምቢ ለከፋፋይ ማለት ይጠበቅባችኋል። ይህን ታደርጉ ዘንድ ጠቅላላው የኢትዮጲያ ሕዝብ በተስፋ እየጠበቃችሁ ነው። መለስ ዜናዊ ባንድ ወቅት “ ሃበሾቹ ቢኖሩም አይጠቅሟችሁም፣ ቢጠፉም አይጎዷችሁም” ሲል የተናገረውን ማስታወስ ተገቢ ይመስለኛል። ሃበሾቹ ያላቸው እኛን ኢትዮጲያዊያን ወገኖቻችሁን ነው። የመለስን ቅጥፈት፣ የመለስን መርዘኛ አስተሳሰብ፣ የመለስን ዕብሪትና ጥላቻ የመረዳት ሃላፊነት ከእንግዲህ የናንተና የናንተ ብቻ ነው።የኢትዮጲያ ሕዝብ ይህን ክፉ መንፈስ ለ25ዓመታት ሙሉ ተዋግቶ እዚህ ደርሷል። ከዚህ በኋላ ትግሉን ላለመቀላቀል ምንም አይነት ምክንያት ልታቀርቡ አትችሉም። እንደማንኛውም ኢትዮጲያዊ ዜጋ በእኩል የመኖር፣ የማደግ፣ የመበልጸግ፣ ከቦታ ቦታ ተዘዋውሮ የመማር፣ የመስራትና ፋብሪካዎቻችሁ ያመረቱትን እቃዎች እንደልብ ለ95ሚሊዮን ሕዝብ ገበያ የመሸጥና በሕግ የመክበር ዋስትና የምትሰጣችሁ ትልቋ እናት ሃገራችሁ ኢትዮጲያና የኢትዮጲያ ሕዝብ እንጂ ሕወሃት ሊሆን ፈጽሞ አይችልም። ሕወሃት የተወሰነውን የትግራይ ሕዝብ በስጋዊ ሕይወቱ ለጊዜው አደላድሎት ሊሆን ይችላል። ዙሪያ ገባውን በግጭትና በተቃውሞ እሳት የሚለበለብ ዓለም ውስጥ እየዘፈቀው የሰላም ደሴት ፈጥሬልሃለሁ ሲለው ግን መጠርጠር ጥሩ ነው። ይህ የሰላም ደሴት የቅዠቶች ሁሉ ቅዠት ነውና። በመንፈሳዊ፣ በስነልቦናዊና በማህበራዊ ሕይወቱ የትግራኡ ህዝብ ከፍተኛ የህሊና ቀውስ ውስጥ እንደገባ ከማንም የተሰወረ ሓቅ አይደለም። የጀርመኑ ሂትለር አገሩንና ሕዝቡን ወደ መቃብር እንደወሰደ ሁሉ ሕወሃትም እንዲሁ ወደ ክፉ መንገድ እየመራችሁ ነውና ቆም ብላችሁ አስቡበት። ባጭሩ ከነአባይ ወልዱ ጋር አብራችሁ አትበዱ! የኢትዮጲያ ሕዝብ ዳግም ለፍቅርና ለአብሮ መኖር እጁን ዘርግቶ በናፍቆት እየጠበቃችሁ ነው።
የሃይማኖት አባቶች፣ ያገር ሽማግሌዎችና ቤተ ዕምነቶች ቀድሞ የነበራቸው ክብርና ይጫወቱ የነበረው የሰላምና የዕርቅ ሚና ከምንጊዜውም በላይ የተሸረሸረበትና እነኚህ ማህበራዊና መንፈሳዊ እሴቶቻችን የተናቁበትና የተዋረዱበት ሰዓት ላይ ደርሰናል። ቅድስት ቤተክርስቲያን ከአጋዚ ጥይት ለማምለጥ መሸሸጊያ ብለው የመጡትን የአዲስ አበባ ዩኒቨሪስቲ ተማሪዎች በፓትሪያርኩ ትዕዛዝ በሯን ዘግታ ወጣቶቹን እንዳስፈጀቻቸው የምናስታውሰው በመንፈሳዊ ዕፍረትና ሀዘን ነው። ከጉራፋርዳ የተባረሩትን ሕጻናትና እናቶቻቸውንም በተመሳሳይ መንገድ ጀርባዋን መስጠቷ የቅርብ ጊዜ አሳፋሪ ታሪኳ ነው። ድምጻችን ይሰማ ብለው በሰላማዊ መንገድ ተቃውሞ ያሰሙ ሙስሊም ወንድምና እህቶቻችን ላይ የደረሰው አካላዊና ስነልቦናዊ ሰቆቃ ጥሎት ያለፈው ጠባሳ የሙስሊሙ ማህበረሰብ ብቻ ሳይሆን የጠቅላላው ኢትዮጲያዊ ቁስል መሆኑን ማስታወስ ይገባል። የኦሮሞ ወገኖቻችን በእሬቻ በዓል ላይ የደረሰባቸውን አሳዛኝ የጅምላ ጭፍጨፋ የምናስታውሰው እንደህዝብ በጋራ የዕፍረትና የቁጭት መንፈስ ነው። ይህ እንዳይደገም ግን ሕልም አለኝ! “ያባቴን ቤት የቁማርተኞችና የወንበዴዎች ቤት አታድርጉት” እንዳለው የጸሎትና የዕምነት ቤቶቻችንን ከወሮበሎችና ከወንበዴዎች አንጽቶ ህዝበ ክርስቲያኑም ሆነ ህዝበ ሙስሊሙ በሰላም አምላኩን የሚያመልክበትን ቤተ ዕምነቱን ዳግመኛ የሚያድሱለት የሃይማኖት አባቶች፣ ጳጳሳት፣ኢማሞችና ፓስተሮች ይመጣሉ የሚል ሕልም አለኝ!  ከምናምንበት አምላካችን ጋራ በዕውነት የምንታረቅበት ጊዜ አሁን ነውና!
አጼ ቴዎድሮስ “ ጥንት ገናና ነበርሽ፣ አሁንም ገናና አደርግሻለሁ!” እንዳሉት አዲሲቷ ኢትዮጲያችን በጀግኖቿ ልጆቿ መንፈስ ዳግም ታድሳ ገናና እንደምትሆን ሕልም አለኝ! አዎን የእናታችን ኢትዮጲያ ማህጸን የጨለማ ንጉሶቹን ሕወሃቶችንና ጀሌዎቻቸውን ብቻ አይደለም የጸነሰው። የኢትዮጲያ ማህጸን አንዳርጋቸው ጽጌን፣ በቀለ ገርባን፣ ኮነሬል ደመቀ ዘውዱን፣ ሳሙኤል አወቀን፣ መራራ ጉዲናን፣ ርዕዮት አለሙን፣ ዩሱፍ ያሲንን፣ አህመዲን ጀበልን፣ አቡበከር መሃመድን፣ ኤርሚያስ ለገሰን፣ ኦባንግ ሜቶን፣ እስክንድር ነጋን፣ ሰርካለም ፋሲልን፣ አንዱ አለም አራጌን፣ ሀሰን መሃመድን፣ አብዱላሂ ሁሴንን፣ ሳዲቅ አህመድን፣ንግስት ይርጋን፣ እማዋይሽ አለሙንና ብርቅዬውን መሪያችንን አርበኛ ታጋይ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋን የመሳሰሉ ዕልፍ አዕላፍ አንበሶችን የወለደ ማህጸን ነው! እናም አርቲስት ቴዲ አፍሮ “ ይሰግዱልሻል የናቁሽ ሁሉ” እንዳለው ኢትዮጲያችን በነኚህ ጀግኖች ልጆቿ ዳግመኛ ገናና እንደምትሆንና ህዝቧ የሚኮራባት አለምም የሚያከብራት እንደምትሆን ሕልም አለኝ!
አንድ ሌላም የመጨረሻ ሕልም አለኝ! ለዘመናት የኢትዮጲያ ተስፋ የነበረውና ለመለስ ዜናዊና ለህወሃቶች የስልጣን ማራዘሚያ ሆኖ የፖለቲካ ቁማር መጫወቻ የሆነውን የአባይን ግድብ እንደምንገነባና ያገራችንን ህዝብ የሚያሰቃየውን የመጠጥ፣ የመብራትና የመስኖ ችግር የምናቃልልለት ጊዜ ሩቅ እንደማይሆን ሕልም አለኝ! አዎን የአባይ ግድብ በኛ ዘመን ይጠናቀቃል!

ድል ለኢትዮጲያ ሕዝብ

አንድነት ሃይል ነው!




በአሜሪካዊው የሰላማዊ ትግል መሪ በዶክተር ማርቲን ሉተር ኪንግ “ I have a Dream” ከተሰኘው ንግግር መንፈስ የተጻፈ

Åpne brev til kronprins Haakon og kronprinsesse Mette-Marit


Fra etiopisk flyktning i Norge
Kjære kronprins Haakon og kronprinsesse Mette-Marit
Vi etiopiske flyktninger i Norge har hørt at du skal reise til Etiopia fra 7-9 november. Vi setter pris på deres innsats i Etiopia. Som dere vet er Etiopia i ferd med å oppleve store etniske konflikter etter 26 års diktatorskap, der bare Tigre folk kontroller økonomisk og militærmakt. Vesten har snudd ryggen mot etiopisk folk og valgte å støtte Tigray minoritet diktatoriske regimet i Etiopia i navn av "strategisk interesse" og "kamp mot Alshabab i Somalia". 85 millioner mennesker ble ofret av vesten for politisk interesse i Afrikas horn. Vi vet at Dere Kronprinsparet ikke er politikere, vi vet også at Dere er visjonære person med rettferdighetssans. Vi tror at Dere kan stå ved siden av det etiopiske folket framfor det brutale regimet som styrer landet ved å kneble opposisjoner i 26 år. Vi har en inderlig tro at Dere Kronprinsparet kan bruke anledningen til å lage en historie som den Bibelske Esther ved å støtte etiopiernes kamp for demokratisk styre som inkluderer alle partier og stammer. Historie vil alltid husker Dere for å ha stått ved siden av undertrykt og forrådt Etiopiere av Vestlige landene.
Folk i Etiopia sier nok er nok; Oromo, Amhara, Gambella osv alle krever demokratisk styre. Det er mange selskaper og politikkere som profiterer fra samarbeidet med diktatorisk regimet og prøver å overtale dere at det etiopiske Tigray regimet gjør godt, det er bare løgn og ondskap. I 1937 Folkeforbundet har forrådt Etiopia da vi ble invadert av Italia men vår Gud har kjempet for oss og det ble en skammelig historie for Folkeforbundet og medlemslandene. Vi ønsker minst Kronprinsparet i Norge gjør noe annerledes enn resten av vestlige land i disse mørkeste dager for etiopiere. Dere kan bruke deres posisjon til å fortelle sannheten at Etiopia trenger demokrati, der vi velger våre egne ledere. Dere kan være stemme til opposisjonsledere, journalister og intellektuelle som lider i fengsel. Etiopia og det etiopiske folk trenger akkurat nå som den Bibelske Prinsen Moses og den bibelske dronning Esther som vil gjøre en forskjell. Vi vet at Dere er i stand til! Det er en sannsynlighet at Tigray regimet faller neste gang Dere reiser til Etiopia og vi flyktninger i Etiopia reiser sammen med Dere til et land der ingen kommer til makten uten valg.
Gud velsigner Dere!
 Mvh
Etiopisk flyktning i Norge