Thursday, December 8, 2011

የኢትዮጵያ ሕዝብ የዜግነት መብቱን ለማስክበር በተቀናጀ መንገድ መነሳቱን ወያኔ ሊቀበል ይገባል ! !

የሀገራችን ህዝብ በዘውዳዊው አገዛዝ ሁለንተናዊ የዜግነት መድሎ አንገፍግፎት በቁጣ በነቂስ በመውጣት በቃ ካለ በኃላ የተሻለ የፖለቲካ ስርዓት በሀገሪቱ ለማስፈን ትልም አለን ባሉ የደርግ ታጣቂ ኃይላት መዳፍ አገሪቱ ከወደቀችበት የዛሬ ፵ ዓመት አካባቢ ጀምሮ ህልም እንጅ አስከ አሁን እውን ባልሆነው የዲሞክራሲ ስርዓት ጥማት እየተቃጠለ ይገኞል፤፤

በሀገራችን የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታን አዘቅት ውስጥ በመጣል ሂደት የጠራ ሀገራዊ እራዒ ሳይሰንቅ የሀገሪቱን ሕዝባዊ አንድነት በማናጋት ጥቂቱን የህዝብ ክፍል ለመጥቀም መሰረቱን የሀገሪቱን ሃብት ዘረፋ እና ንጹሀን ዜጎችን  መግደል አድርጎ የተቋቋመው  ህወሓት  ኢህአዳግ  ትልቅ ሚና ተጫውቱዋል ኢየተጫውተም ይገኛልእ።

 ህወሓት ያኔ ከጅምሩ በተፀናወተው የዘረፋ እና የመገደል አባዜ ቆምኩለት የሚለውን  የህዝብ ወገን እንኳን ሳይቀር በወቅቱ እኔን የለከፈ ጋኔን አልተፀናወታቹም እያለ ንጹሃን ዜጎችን ጭምር እንዳሻው ሲያስር ሲያፍን ሲግድልና የህዝብ ደም በከንቱ ለሴይጣናዊ የማፈራረስ አላማው ሲያፈስ እራሱን ያጎለበተ የጭራቆች ስብስብ ድርጅት መሆኑን ሀገር ወዳድ ሁሉ ልብ ያለው እውነት ነው።

ደርግን ለመጣል በተደረገው ጦርነት ውቅት በህዝብ ስም ተደራጅቶ እንዴት በተወሳሰበ እና ዘመናዊ በሆነ መልኩ አገርንና ህዝብን መዝረፍ እንደሚቻል ጠንቅቆ እራሱን ያደራጀው መለስ ዜናዊ የዘረፋ አድማሱንና የአደረጃጀት ዜዴውን አብረውት ለአላማ ታገልን የሚሉት ወንበዴ አጋሮቹ እንኳን ባልግባቸው ውስብስብ አደረጃጀት በማቀናበር የቻለውን ገድሎ ( አስገድሎ) ያልቻለውን አንገዋሎ ቀሪዎቹን ለአገር ማፍረስ እና ዘረፋ አላማ ይሆኑኛል ያላቸውን የተራቡ የበርሃ ቁንጫዎች በመላ ሀገሪቱ የዛሬ ፳ ዓመት አካባቢ በመበተን የሃገራችን ሕዝብ የተራበውን  እውነተኛ ዲሞክራሲያዊ ስርዓትና  የህግ የበላይነት የሚከበርበትን መንገድ በስለላ አና በተደራጀ የጦር ኃይል እያሽመደመደው ይገኞል።

ይህ ከላይ የጠቀስኩት የተራቡ ቁንጫዎች ስብስብ ሚስጥራዊ አላማ ሳይረዱ የሚያጨበጭቡ ጥቂት ቅንቅኖች ከህዝብ ውስጥ በመያዝ   የማይሞላውን የደም ገንቦ በጉያው ሸጉጦ በመልካም አስተዳደር እጦት ውስጥ አርሮ የሚሰቃየውን ሕዝብ እራሱ ፈጥሮ ለራሱ  በማይገዛበት ህግመንግስት ስምና እና ነጋ ጠባ በሚያወጣቸው አዋጆች በመጠቀም ሕዝብ መፈናፈኞ በማሳጣት እየቦጠቦጠው ይገኞል።

ምንም እንኳን ህዝባችን በአሁኑ ሰዓት እስከ መንደር በወረደ የጥላቻና ሽብር በተሞላው መርዘኛ በሆነውና እንደ መዥገር ህዝብ ውስጥ በተለጠፈው ኢሀደግ ፕሮፓጋንዳ  እንዲሁም እንደ ጉንዳን ህዝብ ውስጥ በሚርመሰመሱ የድርጅቱ ሰላዮች ከምን ጊዜውም በላይ ቢታጠርና መፈናፈኛ ያጣ መስሎ ቢያደፍጥም ፈንቅሎ ለመውጣት ቋፍ ላይ እንዳለ ዘረኛው ህወሓት (ኢሀደግ)መንግስት ማወቅ የተሳነው አይመስለግኝም። 

ከዚህም የተነሳ ይመስላል አባወራው መለስና ጭፍራዎቹ ያዳፈኑት የመሰላቸው የህዝብ ቁጣ በአሁኑ ሰዓት ሲያጎመራ በማየታቸው የተቃዋሚ አባላትና ጋዜጠኞች ላይ ሰፊ የእስርና የአፈና እርምጃ የቀጠለበት ሁኔታ እንዲሁም  በቅርቡ ባወጣው የህዝቡን የአንድነት መንፈስ ሁለንተናዊ በሆነ ይዘቱ የሚያናጋውን የጸረ ሽብር አዋጅ መሳሪያ በማድረግ የህዝብ ብሶት እና ምሬት የወለዳቸውን የፖለቲካ ድርጅቶችንና አንዳንድ የሀገር ተቆርቋሪ ዜጎችን፥ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ አባሊትንና የነፃው ሚዴያ አባላት ሳይቀር አሸባሪ በማለት እስር ቤት መወርወርና ማዋከብ   የስርአቱ የቀን ተቀን ስራ ያደርጉት።

በትንሹ ህወሓት (ኢሀደግ) በራሱ እና ለራሱ ያወጣውን የሀገሪቱን ህገመንግስት እንዲያከበር ጥያቄ ያነሱ የህዝብ ልጆች አና በኑሮ ውድነትና በመልካም አሰተዳደር ዕጦት የተማረረ ህዝብ በሰሜን አፍሪካና በመካከለኛው ምስራቅ ያለውን ህዝባዊ እንቅሰቃሴ ፈለግ ይከተላል በሚሌ ስጋት ብቻ ሁሉን በአሸባሪነት መድቦ ዜጎችን ማሰቃየቱ አገዛዙ ያለበትን የፖለቲካ ውድቀት አመላካች መረጃ ነው።

እንደው  ዝም ብዬ አሁን ያለውን የአገዛዙን ቁንጮ የእድገት ደረጃ ሳስተውለው ያኔ ኮ/ል መንገስቱ ኃ/ማርያም ሀገር ጥለው መፈርጠጫቸው ሰሞን ካሳዩት ቡዙ ባህሪዎች ጋር የሚመሳሰል ቡዙ ነገር አስተዋልኩ። በአሁኑ ሰዓት አባወራው በየመድረኩ የህዝብ ደም ያዞራቸው እስኪመስል ያጓራሉ ይደነፋሉ ጠረጴዛ ይመታሉ ሲሻቸው መርማሪ ፖሊስ ወይም ከሳሽ አቃቤ ህግ ሞቅ ሲላቸው ደግሞ ዳኛ ይሆናሉ ፤ ለሳቸው አስቤ ሳዝን ደግሞ ሌላ ጉድ ነው የሚያስብል ነገር አስተዋልኩ ያም ለሀለቃቸው የዛር ለሚመስለው ድንፋታ ጭፍሮች ያጨበጭባሉ አዳራሹን ያለ ተቀናቃኝ ሞልተው በሚያስለቅሰው ውድቀት ይፍነከነካሉ በርታ እያሉ ወደ ማይቀረው  ህዝባዊ እንቅሰቃሴ አና የቁጣ ማእበል ሲነዱ አየሁና ሽነጥ ቢለኝ በውስጤ እልል አልኩ።

በአሁኑ ሰዓት የሀግራችን ህዝብ በኑሮ ውድነትና በመልካም አሰተዳደር ዕጦት በቃ ብሎ በራሱ ከወሰነ ውሎ ያደረ እና ገንፍሎ በመውጣት ይህንን ለ፳ ዓመታት እንደ መዥገር ከጉያው የሚቦጠቡጠውን ስርአት ከነጭፍሮቹ ለማስወገድ ቁርጠኛ መሰርት ላይ መሆን ማስተዋል አያዳግትም። በስላማዊ መንገድ መብቱን ጠይቆ ሰሚ ቢያጣ ለአገዛዙ ያለውን ጥልቅ ጥላቻ በራሱ ላይ ነዳጅ አርከፍክፎ ለህዝብ ዲሞክራሲያዊ መብት መከበር መስዋትነት እስከመክፈል ደርሷል። 
እንግዲ ልብ ያለው ልብ ይበል እንዲሉ በማወቅም ሆነ ሳታውቁ በክህደት እራሳቹሁን ከዚህ ጸረ ኢትዮጵያ አገዛዝ ስርአት ጋር ያስተሳሰራቹ አይነ ልቦናቹሁን ወደ ህዝባቹ በጊዜ መመለስ የብልህ ውሳኔ ያስብላለልና ተጠቀሙብት።

የኢትዮጵያ ሕዝብ ከተገዥነት አልፎ በዜግነት ደረጃ የሚታይበት ሕዝቡ ገዥዎች በቸርነታቸው ከሚወረውሩለት የመብትና የደህንነት ፍርፋሪ ውጭ በዜግነቱ ሊጠይቃቸው የሚገቡ መብቶችን በማንገብ በቃ ብሎ መነሳቱና በተቀናጀ መንገድ
ሲያደርገው የቆየው ትግል በአሁኑ ወቅት ከፍተኛ ደረጃ ላይ ያደረሰው መሆኑ ተስተውሎ ሁሉም ሀገር ወዳድ ለተፈጻሚነቱ ሊተጋ ይግባል።

By ANARA FA.


No comments:

Post a Comment