Saturday, August 11, 2012

ተመስገን ደሳለኝ “ተከሶ ጉዳዩ በዝግ ችሎት መታየቱን” ከሬድዮ ፋና ሰማ!

 ተመስገን ደሳለኝ ዛሬ ምሳ እየበላ ሳለ የአትሌቶቻችንን ወሬ ለመስማት ጆሮውን አቆብቅቦ ዜና እየተከታተለ ባለበት  “በዛሬው እለት በከፍተኛው ፍርድ ቤት ሶስተኛ ወንጀል ችሎት ክስ እንደቀረበበት እና ክሱም በዝግ ችሎት እንደታየ ተከሳሹ ግን በፍርድ ቤት እንዳልተገኘ” ሲዘገብ ሰማ!
ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ምንም መጥሪያም ሆነ የክስ “ቻርጅ” ሳይሰጠው ፍርድ ቤት ጉዳዩን በዝግ ችሎት አየው መባሉ ክፉኛ እንዳስደነገጠው ነግሮኛል።
የቀረቡበት ክሶችም የሚከተሉት ናቸው፤
1ኛ ወጣቶች በአገሪቱ መንግስትና ህገ መንግስታዊ ስርአቱ ላይ እንዲያምጹ የመገፋፋትና ግዙፍ ያልሆነ የማሰናዳት ተግባር፣
2ኛ የሀገሪቱን መንግስት ስም ማጥፋት እና የሀሰት ውንጀላ እንደሁም
3ኛ የሀሰት ወሬዎችን በማውራት ህዝብን በማነሳሳት ወይም አስተሳሰባቸውን ማናወጥ የሚሉ ናቸው።
የህግ ዕውቀት ያለው ወዳጃችን ዘላለም ማልኮም ክብረት እንደተነተነው ተመስገን በአንደኛው ክስ ከሶስት አመት እስከ ሞት በሁለተኛው ክስ እስከ ስድስት ወር እንዲሁም በሶስተኛው ክስም እስከ ሶሰት አመት የሚደርስ ቅጣት ሊበየንበት እንደሚችል አንቀፅ ጠቅሶ አብራርቶልናል።
እኔ እንደገረመኝ ደግሞ በተለይ “የህብረተሰቡን አስተሳሰብ ማናወጥ” የሚለው ክስ ምንማለት ነው!? ተመስገንም “እነዚህ ሰዎች አጋንንት አደረጉኝ እንዴ!?” ብሎ ሳይደነቅ አይቀርም። ለመሆኑ የህብረተሰቡ አስተሳሰብ ነው የተናወጠው? ወይስ የሰዎቻችንን አስተሳሰብ ነው የተናወጠው!? “ጉድ ሳይሰማ ሰኞም ላይመጣ እኮ ነው ጎበዝ!”
source : http://www.abetokichaw.com

No comments:

Post a Comment