Friday, February 17, 2012

የዘር ማጽዳት (Ethnic Cleansing) ዘመቻ፡ በወልቃይትና በጠገዴ ማህበረሰብ ላይ!

የተባበሩት መንግሥታት ም/ቤት በ1948ና በ1992 ዓ.ም የዘር ማጥፋትንና የዘር ማጽዳትን ወንጀሎች አስመልክቶ ያስተላለፈው ውሳኔ ለዚህ ጦማር እንደ መግቢያ ያገለግሉ ዘንድ የተመረጡ ናቸውና በቅድሚያ የሚከተሉትን ሊንኮች ይመለከቱ ዘንድ በአክብሮት ተጋብዘዋል፡፡
የትግራይ ነፃ አውጪ ግንባር ይህን ኢትዮጵያዊ ዘር ማፅዳት ለምን አስፈለገው? 
ከዚህ ቀደም በተለያዩ መድረኮችና መጣጥፎች እንደተገለጠው ሁሉ ወያኔ በጎንደር ህዝብ ላይ በተለይም በወልቃይት ጠገዴና ጠለምት ህዝብ ላይ የፈፀመው ወረራ በሁለት መሰረታዊና እኩይ ጭብጦች ላይ ይነሳል፡፡
1ኛ. ለታለመው የ“ታላቋ ትግራይ” ና ለ“ትግሪያዊው ወርቅ” ህዝብ የምግብ ዋስትና የሚያረጋግጥ ለም መሬት በመፈለግ ሲሆን፤
2ኛ. ለወደፊት በ“ሃገርነት” ለታጨችው ለ“ታላቋ ትግራይ” ከቀሪው አለም ጋር የየብስ የመውጫና የመግቢያ  በር ለማግኘት በመቋመጥ የተተለመ ነበር፡፡
ታዲያ ከዚህ ስግብግባዊ ቅዠት በመነሳትና  ይህን እኩይ የወረራ አላማ እውን ለማድረግ ሁለት አበይት እቅዶችን ለመከተል ወደው ነበር፡፡ ወደ እቅዶቹ ዝርዝር ታሪክና አፈፃፀም ከመግባታችን በፊት ግን ለግንዛቤ ይረዳ ዘንድ በቅድሚያ እጅግ በአጭሩ ወረራ ስለተደገሰለት ወገናችን በተለይም ስለወልቃይት ጠገዴ ማህበረሰብና አካባቢ ትንሽ በአይነ ህሊናዎ እናስቃኝዎ፡፡
ይህም ታሪካዊ እውነታ በ1968 ዓ.ም. የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጭ ግንባር (ወያኔ) ባወጣው ማኒፌስቶ መሰረት የጠለምት፣ የወልቃይትንና የጠገዴ መሬቶች በ“ታላቋ ትግራይ” ካርታ ውስጥ እንደሚጠቃለል በግልፅና በዝርዝር ያሳያል። ለግንዛቤ ይረዳዎ ዘንድ እባክዎ ኪዚህ በመቀጠል የተያያዘውን ሊንክ በመጠቀም የወያኔ ማኒፈስቶን ይመልከቱ፡፡ 

  ምንጭ:      http://www.ecadforum.com/Amharic/archives/1903 :

No comments:

Post a Comment