Wednesday, April 18, 2012

አንድ-ዶላር-በኻያ-ብር-ሊመነዘር-ነው


አዲስ ነገር ኦንላይን ምንጮች በዚህ ሳምንት እንደገለጹት ብሔራዊ ባንክ በሚቀጥሉት ጥቂት ሳምንታት የብርን የአሜሪካ ዶላር የመግዛት አቅም በ15 በመቶ ያህል ለመቀነስ ተዘጋጅቷል፡፡ በዚህም በሰሞኑ መደበኛ የምንዛሬ ገበያ በአማካይ በብር 17.35 ሲገዛ የነበረው የአሜሪካን ዶላር በብር 20 ሊመነዘር ይችላል፡፡
የኢትዮጰያ መንግሥት በተለይ ካለፉት አራት ዓመታት ወዲህ እየተባባሰ የመጣውን የውጭ ምንዛሬ እጥረት ለመቅረፍ አልተቻለውም፡፡ ስለዚህም በዓለም አቀፉ ገበያ የዋጋ ተወዳዳሪነትን ይጨምራል፤ በዚህም የውጭ ምንዛሬ ክምችት ተያይዞ ያድጋል በሚል በተደጋጋሚ የብርን የመግዛት አቅም ማሽመድመድን ብቸኛው አማራጭ አድርጓል፡፡ ባለፈው ዓመት በተመሳሳይበወሰደው እርምጃ የብርን የምንዛሬ ዋጋ በ20 በመቶ አውርዶት ነበር፡፡ ይኹንና የታሰበው የገቢ ንግድ ሳይጨምር የዋጋ ግሽበት ከነበረበት ከፍተኛ ምጣኔ እየገሰገሰ የኑሮ ውድነቱን አባብሶታል፡፡አዲስ ነገር ኦንላይን ምንጮች በዚህ ሳምንት እንደገለጹት ብሔራዊ ባንክ በሚቀጥሉት ጥቂት ሳምንታት የብርን የአሜሪካ ዶላር የመግዛት አቅም በ15 በመቶ ያህል ለመቀነስ ተዘጋጅቷል፡፡ በዚህም በሰሞኑ መደበኛ የምንዛሬ ገበያ በአማካይ በብር 17.35 ሲገዛ የነበረው የአሜሪካን ዶላር በብር 20 ሊመነዘር ይችላል፡፡የኢትዮጰያ መንግሥት በተለይ ካለፉት አራት ዓመታት ወዲህ እየተባባሰ የመጣውን የውጭ ምንዛሬ እጥረት ለመቅረፍ አልተቻለውም፡፡ ስለዚህም በዓለም አቀፉ ገበያ የዋጋ ተወዳዳሪነትን ይጨምራል፤ በዚህም የውጭ ምንዛሬ ክምችት ተያይዞ ያድጋል በሚል በተደጋጋሚ የብርን የመግዛት አቅም ማሽመድመድን ብቸኛው አማራጭ አድርጓል፡፡ ባለፈው ዓመት በተመሳሳይ በወሰደው እርምጃ የብርን የምንዛሬ ዋጋ በ20 በመቶ አውርዶት ነበር፡፡ ይኹንና የታሰበው የገቢ ንግድ ሳይጨምር የዋጋ ግሽበት ከነበረበት ከፍተኛ ምጣኔ እየገሰገሰ የኑሮ ውድነቱን አባብሶታል፡፡የኢትዮጵያ ትልቁ የኢኮኖሚ አውታር (ማክሮኢኮኖሚ) በዋነኝነት በግብርና ምርቶች ዋጋ መውደቅ እና መነሳት እንዲሁም በውጭ ምንዛሬ ዋጋ መውጣት እና መውረድ የሚገለፅ በመኾኑ፣ በውጭ ምንዛሬ ለውጡ በአብዛኛው ተጎጂ የሚኾነው ከፍተኛውን ሸመታ በምግቦች ላይ ያደረገው ዝቅተኛ ገቢ ያለው የኀብረተሰብ ክፍል ነው፡፡ ባለፉት ጥቂት ወራትም እንደተስተዋለው የብር የመግዛት አቅም እየወረደ መምጣት መሠረታዊ በሚባሉ ሸቀጦች ላይ ከፍተኛ የዋጋ ለውጥ እንዲከሰት በማድረግ ኑሮ የበለጠ ድኻውን እንዲጫነው አድርጓል፡፡የአዲስ ነገር ኦንላይን ምንጮች እንደሚገልጹት ከሆነ በዚህ ወቅት በአውሮፓ የሚስተዋለውየኢኮኖሚ አለመረጋጋት በቀጣዮችም ወራት የብርን የመግዛት አቅም እንደሚገዳደረው ይጠበቃል፡፡ በተለይ ከፍተኛ ገቢ እንደሚያመጣ ይጠበቅ የነበረው አበባ ገበያው እየቀዘቀዘ መምጣቱ በቀጣይ ይደረጋል ተብሎ የሚጠበቀውን የምንዛሬ ለውጥ ትርጉም አልባ ሊያደርገው ይችላል ፡፡የብር የመግዛት አቅም እየተመናመነ መምጣት የውጭ ምንዛሬን ዝቅ ከማድረግ በተጨማሪ መንግስት ከፍተኛ ምጣኔ ያላቸውን የብር ኖቶች ወደ ገበያው ለማስገባት እቅድ ይዟል፡፡ ለዓመታት ከፍተኛው የመገበያያ ኖት ኾኖ ሲያገለግል የቆየው የ100 ኖት የዋጋ ግሽበት የፈጠረበትን ጫና መቋቋም ባለመቻሉ በቅርቡ የ200 ብር ኖት ወደ ገበያው እንዲገባ ይኾናል፡፡


የኢትዮጰያ መገበያያ ገንዘብ እያደር እያገረሸበት የመጣውን የዋጋ ግሽበት መሸከም አልቻለም፡፡ በአገር ቤት የሚካሄዱ ግብይይቶችን ለማካሄድ ያለው አቅም እየዛለ፤ የአሜሪካ ዶላርን ከመሰሉ የዓለም አቀፍ መገበያያ ገንዘቦች ጋር ያለው የምዛሬ ዋጋ ደግሞ እየቀነሰ መጥቷል፡፡ ባለሞያዎቹ ልቅ-ውድቀት (Free fall) የሚሉት አይነት የውጭ ምንዛሬ ዋጋ መቀነስ እየተስተዋለ ነው፡፡ መፍትሄዎች ሁሉ የተሟጠጡበት የሚመስለው ብሔራዊ ባንክም ከብር ጋር መታገልን የመረጠ ይመስላል፡፡
ባለፉት ጥቂት አመታት እንደተስተዋለው በምንዛሬ ለውጡ አብዛኛው ድኻ ቢጎዳም ወቅቶችን እየጠበቁና ዶላርን እያከማቹ በኢ-መደበኛው ገበያ ለሚሸጡ ነጋዴዎች ሰርግና ምላሽ ነው፡፡ ትላንት በዝቅተኛ ምንዛሬ የሰበሰቡትን የውጭ ምንዛሬ የዋጋ ለውጡን ተከትለው እስከ ኻያ በመቶ ያህል ትርፍ ሊሰሩበት ይችላሉ፡፡
source ;http://addisnegeronline.com/2011/10/አንድ-ዶላር-በኻያ-ብር-ሊመነዘር-ነው/  

No comments:

Post a Comment