Wednesday, August 29, 2012

በመለስ አጥንት ይሁንባችሁ፣ አለ በረከት ስሞኦን


ሄኖክ የሺጥላ
የሰሞኑ ዜና እንደ እስር ቤት ወጥ ድብልቅልቅ ያለ ስሜት ይፈጥራል አይደል? ካንዱ ዜና ወደ ሌላው ስሄድ በቃ ግራ ገባኝ… ETV በቃ  ስራ ጀመረ::  እኔ እንደውም ከአሁን በሁዋላ ኢሳትን አልመለከትም::  ምክንያቱም ETV ይግደለኛ::
በመጀመሪያ አቡነ ጳውሎስ እንደ ልደት ኬክ መስታወት ውስጥ ሆነው ብቅ አሉ:: happy birth day የሚል ነገር ለማንበብ ሳተኩር… አንድ  ኮስተር ብሎ የተኛ  ነገር ተመለከትኩ… እንደ አጋጣሚ የኮምፒዩተሬ ድምጽ ማውጫ  (Speaker) ስለተበላሸ… ምስሉን ብቻ ነበር  የተመለከትኩት::
ጥቁር  በጥር የለበሱ ሰዎች ይጋፋሉ… ኮምፒውተሬ ዝም ስላለ ነው መሰለኝ ተጋፉ ተብለው ሁሉ የታዘዙ ነው የሚመስለው::  የስፔኖች አመታዊ ሰንጋን የማሩዋሩዋጥ በዓል ትዝAbune Paulos funeral in Ethiopia አለኝ::  የእጣ ፈለግ የሚለውን መጽሃፍ አጎቴ  ህጻን ሁኜ ነበር ያነበበልኝ… እና  ሰንጋውን  ቀድመው ለመሮጥ  የሚሞክሩ እስፔናዊ ጀግኖች::  ይቺ ዜናማ አታመልጠኝም ብዬ ማዳመጫዬን እንዲሰራ አደረኩት::  ድራይቨር የሚባል ነገር ስለሌለው ነው አለኝ አንድ ወዳጄ::  ምን ድራይቨር አለ ሁሉም በነቂስ ቀብር ወጥተዋል እኮ! እና ቀጠለ… የተኛ ኮፍያም አብሬ አየሁ… እንዴ ባለኮፍያ ኬክ  መጣ እንዴ ብዬ ሳልጨርስ ለካስ አባታችን ናቸው:: በሞትኩት…  ሁኔታው ሁሉ  “ደረሰ ደረሰ እየገሰገሰ” የሚለውን የዝሆን ተንቦላ ሎተሪ ማስታወቂያ  አስታወሰኝ::  በቃ ጋሼ ዝሆን ብር ጭኖ ከልበስ ከልበስ ይላል… እናቴ ደሞ ቆርጫለሁ ምናምን ብላ ታወራለች… አጎቴ “እስኪ ቁጥርሽን አሳይኝ ይላታል”… እሱዋ ደሞ “አላሳይም ትላለች”.. ቀበል ያደርጋትና… “ገና ላልወጣ ሎተሪ ይላታል”… በቃ ያ ሁሉ ትዝ አለኝ… ትከተለውና  ”በህልሜ አይቼአለሁ ለኔ ነው የሚወጣው ትላለች”… “እስቲ ቁጥሩን በቃልሽ ንገሪኝ በህልምሽ ካየሽው” ይላታል… ቆጣ ትልና… “ሲወጣልኝ ብቻ ነው ያየሁት” ተላለች::  ይገርማል… እኔም የናቴ ተጋብቶብኝ ነው መሰለኝ  “በህልሜ አይቼ ነበር… ማለቴ አባታችን ሲሞቱ… ግን ሲቀበሩ አብሬ ስላላየሁ  ኢንዲህ የልደት ኬክ መሰሉኝ  እንጂ”::
ዜናው ቀጠለ… ወይዘሮ አዜብ ዛሬም ያለቅሳሉ… እንግዲህ ትናንት ትቻቸው የሄድኩ ማለት ነው:: የነ ነብዩን የነ ሽብሬን የነ አስራት ወልደየስን ውዘተ ደርባ ደራርባ ካልሆነ በስተቀር  ለመሌ  መቼም እንደ ፈንዲሻ ለያዠ ለገራዡ አስቸግራ ቦሌ አየር ማረፊያ ላይ ታች ያለችው ይበቃት ነበር:: ግን ምን ታርገው… :: አንባቢያን እዚህ ጋ እኔ ብቻዬን ግብዝ ስለሆንኩ ይቅርታ አድርጉልኝ… ብዙ ተጠንቅቀው የሚናገሩ አንደበተ ርትኡዎች አሉና:: እናላችሁ ዜናው ቀጠለ…. “በየቀበሌው ድንኩዋን ተተከለ” ነጭ ጤፍና ጥቁር ሸሚዝ ዋጋው ጨመረ…ሃገሪቷ ጥቅር በጥቁር ሆና የሬሳ ሳጥን ሻጮች “እኛ በገላችን ነው አሉ” ቀጠሉና… ለኛ የሚያዋጣን ካድሬዎች ቢሞቱ ነው… ንጉስና ጳጳስ ሲሞት ከመጉዋጉዋት ሌላ ምንም አይተርፈንም ዐሉ:: እንግዲህ እንደ ሃይሌ አያያዝ ከሆነ ገድ ሳይላችሁም አይቀር… እናንተ ብቻ አጥብቃችሁ ጸልዩ! እና እንዳልኩዋችሁ ዜናው ቀጠለ… አቶ በረከትም ትኩስ ሬሳ አስቀምጠው “በመለስ አጥንት ይሁንባችሁ” አሉ እኔም ጆሮዬን ማመን አቃተኝ :: አያያዙን አይተህ ጭብጦውን ቀማው ነው የሚሉት እነዛ ዘመዶቼ ሌላ ታዲያ ምን ይባላል:: በልጅነቴ አያቴ…”በልሃ ልበልሃ” ይሉልኝ ነበር… እና ሰውየው በሬው ጠፍቶ.. የት እንደገባ ለማወቅ ደፋ ቀና ሲል… አንዲት ህጻን ልጅ አጥንት ስትግጥ ያያታል…. እናም የልጅቱዋን አባት አውጫጭኝ (አፈርሳታ) ላይ ይሞግተዋል:: ሃሳቡ..” ልጅህ የምትግጠው የበሬዬን አጥንት ነው”… ሲሆን… ተከሳሹም… ሲመልስ…”አንድ ፍሬ ናት የኔ ልጅ… የወደቀ አጥንት አንስታ ብትግጥ ምን ይገርማል አለው”::  እውነቱን ነው… አቶ በረከት የወደቀ አጥንት አንስተው ቢግጡ ዛሬ ማን ይሰማል ብለው ነው:: በአጥንት ቢሉ: በስጋ ቢሉ: በድልህ ቢሉ: በቁዋንጣ ቢሉ: በቄራ ቢሉ ማ! ይሰማል:: ከፈለጉ አጥንቱን እንደ ዴንጀር ምልክት ስለው ለእንቁጣጣሽ እንዲሰጥዎ ከፈለጉ ምን ቸገረኝ:: እና ዜናው ቀጠለ… ታጋይ መለስም ተባለ… “አፈር ነህና ወደ አፈር ትመለሳለህ”… “ታጋይ ነህና ወደ ታጋይ ትመለሳለህ”….
ቸር ይግጠመን
Henoke Yeshetlla

source:http://www.ecadforum.com/Amharic/archives/4083 

No comments:

Post a Comment