Tuesday, October 30, 2012

ገደሏት እና የሚገሏት የሚበሉባት ሃገር – በአያና ከበደ


አገሬ ኢትዮጵያ ሞኝ ነሽ ተላላ :
የሞተልሽ ቀርቶ የገደልሽ/የሚገልሽ/ በላ::

በአያና ከበደ

Ayana kebed 


ሰላም ወገኖች እንደምን አላችሁልኝ ይህን ግጥም ማን ነበረ የገጠመው?
አዎ አሁን አሁን የሚፈጠሩትን እና ቀደም ብልው የተፈጠሩትን ነገሮች ሳገናዝብ ከላይ የቀረበው ግጥም ትክክለኛ እንደሆነ መረዳት ለማንም ሰው አያዳግትም:: ይህንንም እንደ ማረጋገጫ ባይሆንም በሃይማኖታዊ ቅኔ ወይም በገደምዳሜ በቸኛው የተቃዋሚ የትወካዮች ምከር ቤት አባል አቶ ግርማ ሰይፉ በ አቀርቡት የፓርላማ የንባብ ሪፖርታቸው መዝጊያ ላይ ኢትዮጵያን እግዚአብሄር በበረከቱ ይጎብኛት በማለት የፓርላማ አባሎች ነን የሚሉት ገብቶአችተዉም ይሁን ሳይገባቸው ሲንከተከቱ ኢቲቭ/ETV/አሰምቶናል::
እንግዲህ ከ አቶ ግርማ ሰይፉ መልክት እንደምጠረጥረው እግዚአብሔር የ አቶ በረከትን ልብ ያራራላት እና የተሻለ የፖለቲካ ምህዳር ይምጣልን የሚመስል ውስጠ ወይራ ንግግር እንዴት ለተወካዮች ምክርቤት አባል መሳቂያ እንደሆነ እነሱም የተረዱት አይመስለኝም::

ጉድ እና ጅራት ከወደ ኋላ ነው እንዲሉ አቶ በረከት ደሞ ሰሞኑን በ ኤርትራውያን ተቃዋሚዎች መወያያ ክፍል /Eritrean oppositions Arabic pal talk/ እንግዳ ሆነው ቀርበው ባድመ የ ኤርትራ እንደሆነች እና ኤርትራውያን የተባረሩትም በ አቶ ሰየ አበረሃ :በ አቶ ገበሩ አስራት እና በ አቶ ተወልደ ላይ እጃቸውን ቀስረዋል:: እም እም እም አሉ አለቃ ገብረሃና ከ ኤርትራ ጥርሳቸውን እየተነቀሉ የተባረሩትን ኢትዮጵያዊያን ማ ያስብላቸው ይሁን ነው ዋናው ጥያቄ? እንዴት ነው ይሄ ነገር ትንሽ ስጋ እንደ መርፌ ትወጋ ይሏችኋል ይሄ ነው::

ወደ ዋናው እውነታ ልመለስ እና አሁንም ያች ሃገር እየተመራች ያለችው በሚገሏት ሰዎች እንደሆነ አያጠራጥርም :: ምክንያቱም በተለያየ ጊዜ መገናኛ ሚዲያዎች እና መወያያ ሚዲያዎች ላይ እየወጡ የሚወረውሩት አነጋገርከፈለገን እናፈርሳታለን የሚል ምን ታመጣላችሁ ንግግር በ አንክሮ ሊታየ የሚገባው ጉዳይ ነው:: በ እርግጥ ህዝቧ በአካበተው ልምድ አሁንም በታጋሽነት እና በትግስት ስቃዩን ዋጥ በማድረግ አገሩ እንዳትፈርስበት ከተለያዩ ጠላቶቿ እና ከባንዳዎች ሲጠብቃት እንደኖረው እይጠበቃት እና በተጠንቀቅ እየታገለ እና መሰዋትነት እየከፈለ ይገኛል::
አዲሱ ጠቅላይ ሚንስትር እና ምከትላቸው በተደረገው ምደባ አንደኛው ከደቡብ አንደኛው ከ አማራ ቦታው ላይ መቀመጣቸዉን ዋናው ጠቅላያችን በ ኢቲቭ/ETV/ስለነገሩን እንዝህን ጠቅላዮች እዉነት የሚያገለግሉት ለህዝብ ነው ወይስ ለመዳቢዎቻቸው ነው የሚል ጥያቄ በ ሕዝባችን ዘንድ ማስነሳቱ አልቀረም?

ከአንዳንድ ሁኔታዎች እንደሚታየው ግን ገዳዮቿ ገዥ የሆኑባት ሃገር ጠቅላዮቻችን እንደቀድሞ ባንዳዎች አገልጋይ ሆነው በሕዝብ እና በአገር ላይ በደል እንዳይደርስ የማስጠንቀቂያ መለክቴን አደርሳልሁ::
ስለዚህ ለጠቅላዮቻችን አንድ ከበድ ያለ መልክት ጣል ማድረግ ስለአስፈለገኝ ጠቅላዮቻችን አንድ ከበድ ያለ መልክት ጣል ማድረግ ስለአስፈለገኝ ጠቅላዮቻችን ሆይ ለ አገራችሁ ስትሉ ከሚገሏት እና ከ ገደሏት ጋር አብራችሁ ሃገራችንን መግደል በታሪክም በትውልድም የሚያስጠይቃችሁ እንደሆነ ልትገነዘቡት ይገባል እላለሁ::

በመጨረሻም ኢትዮጵያዊያን ሆነው አገራቸውን ለሚገሏት ዋ ! እኔን እኔን አሉ ቀኛዝማች ሰውነቴ እናተን አያርገኝ እያለሁ ጽሁፌን በታወቁት የጎጃም አርበኛ አባባል እዘጋለሁ ::


No comments:

Post a Comment