ኢ.ኤም.ኤፍ (ልዩ ዘገባ) – በአሁኑ ወቅት የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር ከህክምና አገግሞ ለስራ ባለመብቃቱ፤ በሬዲዮ ፋና በኩል… “ጠቅላይ ሚንስትሩ ከሞተ ማን ተክቶ ይሰራል?” በሚል ርዕስ ሰፊ ውይይት ተደርጎ ነበር። በዚህም ውይይት ወቅት የህግ ሰዎች “በምትኩ ምክትል ጠቅላይ ሚንስትሩ ኃይለማርያም ደሳለኝ ተክቶት ይሰራል” የሚል ትንታኔ ሰጥተዋል። ይህ እንግዲህ በኢህአዴግ ሬዲዮ ፋና በኩል የተደመጠ ነው። በተግባር ግን አሁን የጠቅላይ ሚንስትሩን ቢሮ ስራ እየሰራ የሚገኘው የቀድሞው የኦሮሚያ ምክትል ፕሬዘዳንት የነበረው፣ ሙክታር ከድር መሆኑ ታውቋል።
ሙክታር ከድር የኢህአዴግ ጽ/ቤት ኃላፊ ሲሆን፤ መለስ ዜናዊ ከመታመሙ በፊት የጠቅላይ ሚንስትሩን ቢሮ ሸፍኖ እንዲሰራ ተደርጎ እንደነበር የደረሰን መረጃ አሳውቋል። በአሁኑም ወቅት ሚንስትሮች ግንኙነታቸውን ከምክትሉ ጠ/ሚንስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ጋር ሳይሆን፤ ከሙክታር ከድር ጋር እንዲሆን መመሪያ ተላልፏል። በዚህም መሰረት ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ ኃይለማርያም በውጭ ስራዎች ብቻ ትኩረት እንዲያደርግ በኢህአዴግ በኩል ትዕዛዝ የተሰጠው መሆኑን የደረሰን የውስጥ መረጃ ያሳውቃል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በዛሬው እለት በረከት ስምኦን፤ የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ በተሻለ የጤንነት ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ገልጸዋል። ይህ መግለጫ በኢህአዴግ ሰዎች በኩል መረጋጋትን ሊፈጥር ቢችልም፤ በህወሃት ውስጥ ግን የታፈነ ንዴት ያለ ይመስላል። የዚህም ንዴት መነሻ የሆነው፤ አንድም ስለጠቅላይ ሚንስትሩን የጤንነት ሁኔታ ህወሃት እንደድርጅት በቀጥታ የሚያውቀው ነገር አለመኖሩ ሲሆን፤ በሌላ በኩል ደግሞ (እዚህ ላይ መጥቀስ ባንፈልግም፤ የደረሰንን ሪፖርት እንዳለ ለማቅረብ ያህል) ሙክታርም ሆነ ኃይለማርያም የሌላ ብሄር ተወላጆች መሆናቸው በህወሃት ባለስልጣናት በኩል ግልጽ የሆነ ኩርፊያ እየታየ ነው። ይህም ሆኖ በቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር ስር ይመራ የነበረውን የጦር አዛዥነቱን ሚና ማን እየተጫወተ መሆኑን በቂ መረጃ ለማግኘት አልተቻለም። ከዚህ በኋላ የመለስ ዜናዊ አመራር የሚያከትም ከሆነ፤ ሳሞራ የኑስ እና እና ሌሎች የህወሃት ጄነራሎች የሙክታር ከድርንም ሆነ የኃይለማርያምን ትዕዛዝ የመቀበላቸው ጉዳይ በጥያቄ ውስጥ ይቆያል።
በመሆኑም አሁን ኢትዮጵያ ውስጥ ባለው የጦር አዛዥ ክፍተት ምክንያት… ኤታማዦር ሹሙ (ሳሞራ የኑስ) በከፍተኛ ወታደራዊ ስልጣን ላይ ይገኛል። ይህም ማለት በአሁኑ ወቅት ኤታማዦር ሹሙ የበላይ ኃላፊ ስለሌለው፤ ከምክትሉም ሆነ አሁን ካለው የሙክታር ቢሮ የሚሰጠውን ትዕዛዝ ያለመቀበል አዝማሚያ በግልፅ ይኖራል፤ ይህንን ክፍተት በመጠቀም ሳሞራ የኑስ መፈንቅለ መንግስት የማድረግ ፍላጎት ካለ መፈጸም እንደሚችል ግምት እየተሰጠ ነው።
እስካሁን የህወሃት አባላት ስብሰባ እንዲጠራላቸው እና የመለስ ዜናዊ ጉዳይ እንዲብራራላቸው ያቀረቡት ጥያቄ ምላሽ አላገኘም። አዜብ መስፍን ከአገር እንዳትወጣ የተጣለባት ማዕቀብ እንደተጠበቀ መሆኑን የደረሰን የቅርብ ምንጭ ገልጿል። ወደፊትም የአዜብ መስፍን ህልውና ያለው፤ በመለስ ዜናዊ መሞት ወይም በህይወት መኖር ላይ የተመሰረተ ይሆናል። መለስ ዜናዊ በሞት የሚለይ ከሆነ የአዜብ መስፍን ጉዳይ የሚያበቃለት ብቻ ሳይሆን፤ በጥላቻ ቂም የቋጠሩ የህወሃት ሰዎች ሊበቀሏት ይችላሉ የሚል ስጋት አለ።
source: http://www.ethioforum.org/?p=11665
source: http://www.ethioforum.org/?p=11665
Is this the same Muktar Kedir the man who is responsible for instigating the massacre of Christians in the vicinity of jimma? If that is the same Muktar Kedir; Oh God have mercy for poor Christians.
ReplyDeleteyep he is the same guy. But I doubt this news. I dont think EPRDF will give him this much power.
DeleteMuktar probbaly was told to file letters in their correct location until a new master is assigned. Hailemariam is sent to do the happy errand boy job for berhane g/kirstos. A dog canot sleep on the master's bed.
ReplyDelete