Saturday, August 4, 2012

‹‹ባለቤቴ ያለምንም ማስረጃ ከህጻናት ልጆች ተነጥላ ታስራብኛለች›› ጁነዲን ሳዶ


አውራምባ ታይምስ(አዲስ አበባ) – የኢትዮጵያ የስቪል ሰርቪስ ሚኒስትር የሆኑት አቶ ጁነዲን ሳዶ፣ ባለቤታቸው ለ16 ቀናት ያህል ያለምንም ማስረጃ በመታሰራቸው ከቤተሰቦቻቸው ጋር ለከፍተኛ ጉዳት መዳረጋቸውን ገለጹ፡፡ አቶ ጁነዲን ዛሬ ቅዳሜ በታተመው ኢትዮ ቻናል ጋዜጣ ላይ ባሰፈሩት ጽሁፍ ላይ እንደገለጹት ባለቤታቸው ሳውዲ አረቢያ ኢምባሲ ገብተው ስለወጡ ብቻ ተወንጅለው እስር ቤት መግባታቸው ተገቢ አለመሆኑን በምሬት ገልጸዋል፡፡


‹‹ኤምባሲ ገብታ ስትወጣ በተደጋጋሚ አየናት ከማለት አልፎ ከዚያስ የት ነው የምትሂደው? ገንዘብ ይዛ ወጥታ ገንዘቡን ምን ላይ ነው ያዋለችው? እቤትም ሆነ ውጭ ከነማን ጋር ግኑኙነት አላት? አሩሲ ስትሂድ ምንድን ነው የምታደርገው?›› ብለው መመርመር ነበረባቸው ያሉት አቶ ጁነዲን ‹‹ሌላው ቢቀር ሁልግዜ ከፓሊስ ጥበቃ ጋር ስለምትንቀሳቀስ ፖሊሶቹንም ጠርቶ ማነጋገርና የበለጠም እንዲያጠኑላቸው ማድረግ ሲችሉ ይሄ ሁሉ አልተደረገም ለ16 ቀናት ክህጻናት ልጆች ተነጥላ መታሰሯ በቤተሰቤና በኔም ላይ ከፍተኛ ጉዳት አስከትሏል›› ብለዋል፡፡  በአቶ ጁነዲን እምነት በአሁኑ ሰዓት ከአክራሪነት ጋር በተያያዘ  ፖሊስ በባለቤታቸው ላይ ያገኘው አንዳች ዓይነትማስረጃ የለም፡፡

    No comments:

    Post a Comment