Tuesday, September 4, 2012

የአክቲቪስትና አርቲስት ታማኝ የአውስትራሊያ ቆይታ ጠቅላላ ሪፖርት ለኢሳት ድጋፍ ከ115 ሺህ በላይ ዶላር አሰባአቧል! AUGUST, 2012


የአርቲስታ አክቲቪስት ታማኝ
ላለፉት 8 ዓመታት አገራዊ ፋይዳ ያላቸውንና ለህዝባችን ሁለንተናዊ ነጻነት የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን በመደገፍ ሲንቀሳቀስ የቆየው የሜልበርን ዲሞክራሲ ለኢትዮጵያ ድጋፍ ቡድን ባደረገለት ግብዣ በ 12/08/12 አውስትራሊያ የገባው ተወዳጁና እውቁ የጥበብ ሰው አርቲስት ታማኝ በየነ በአውስትራሊያ 5 የተለያዩ ከተሞች ማለትም በሜልበርን ፤ በሲድኒ፤ በአድላይድ፤ በብሪዝበንና በፐርዝ በተከናወኑ የኢሳት ድጋፍ ማሰባሰቢያ ዝግጅቶች ላይ በመገኘት ከ 115 ሺህ በላይ ዶላር ማሰባሰብ ችሏል።
አርቲስት ታማኝ የመጀመሪያ ዝግጅቱን AUGUST 11 ሜልበርን ከተማ ላይ እንዲያደርግ በተያዘው እቅድ መሰረት ከዋሽንግቶን በመነሳት ጉዞ ቢጀምርም በበረራ መሰረዝ ምክንያት በታቀደው ቀን ሜልበርን ሊገባ አልቻለም። በመሆኑም የሜልበርኑ ዝግጅት ለተከታይ ሳምንት ሊተላለፍ ግድ ብሏል።
ተከታዩን በረራ በመጠቀም ከ20 ሰአታት ረዥም ጉዞ በኋላ እሁድ AUGUST 12 ቀን ማለዳ ሜልበርን የገባው አርቲስት ታማኝ ለአንድ ሰአት እንኳ ሳያርፍ ከሜልበርን ወደ ሲድኒ በመብረር በዛው ቀን በሲድኒ በተደረገው የኢሳት ድጋፍ
ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ላይ ተገኝቷል።
ታማኝ በሲድኒ ባደረገው ዝግጅት እንቅልፍ ማጣትና ረዥሙ ጉዞ ሳይበግረው በሲድኒ ታሪክ ታይቶ የማይታወቅ ብዛት ለነበረው ታዳሚ ድንቅ ዝግጅት እንዳቀረበ በስፍራው የተገኘው ጋዜጠኛ አብይ አፈወርቅ ዘግቧል።በዚሁ ዝግጅት ከአስር ሺህ ዶላር በላይ ለኢሳት ድጋፍ ማሰባሰቡም ታውቋል። የሲድኒን ዝግጅት ሪፖርት እዚህ ማንበብ ይችላሉ
ሁለት ቀናት በሲድኒ አሳልፎ ማክሰኞ ወደ ሜልበርን ተመልሷል። በሜልበርንም ለሁለት ቀናት ቆይቶ አርብ ወደ አድላይድ በመብረር በዛው ቀን ምሽት በተከናወነው የድጋፍ ማሰባሰቢያ ዝግጅት ላይ ተገኝቷል። በአድላኢይድ ዝግጅትም 12 ሺህ ዶላር በላይ ማሰባሰብ ችሏል። የአድላይድን ሪፖርት እዚህ ላይ ያንብቡ
ይህ ብቻ አይደለም የአድላይድ ዝግጅት የተጠናቀቀው ከእኩለ ለሊት በኋላ ስለነበር በማግስቱ በብሪዝበን ለሚደረገው ዝግጅት ለመድረስ ከጥቂት ሰአታት እንኳ እንቅልፍ ሳያገኝ በሚቀጥለው ቀን ማለዳ ወደዛው መብረር ነበረበት። እንቅልፍ ማጣቱ፤ ድካሙና፤ ተከታታይ በረራው ሳይበግረው ቅዳሜ ቀን ከቀትር በኋላ በብሪዝበን ተገኝቶ ባቀረበው ዝግጅት ታዳሚውን ኢትዮጵያዊ ከመጠን በላይ ያረካና ያስደሰተ እንደነበር የዝግጅቱ አስተባባሪዎች መስክረዋል። ታማኝ በብሪዝበንም ከ 16 ሺህ ዶላር በላይ ማሰባሰብ ችሏል።(የብሪዝበን ሪፖርት አልደረሰንም)

page1image16616
page1image16888
page1image17160
የአርቲስታ አክቲቪስት ታማኝ ጉዞ በብሪዝበን ያበቃ አልነበረም። የብሪዝበን ዝግጅት እንደተጠናቀቀ አሁንም ለጥቂት ሰአታት ብቻ አርፎ በማግስቱ ሜልበርን ላይ ለሚደረገው ድጋፍ ማሰባሰቢያ ዝግጅት ለመድረስ ማልዶ ወደ ሜልበርን አቅንቷል።
ይህ ማለት ታማኝ ለሶስት ተከታታይ ቀናት በሶስት ከተሞች በሚደረጉ ዝግጅቶች ላይ ለመገኘት ሶስት በረራዎች ማድረግ ነበረበት።
ከአንዱ አገር ወደ አንዱ አገር በሚያደርገው በረራ መካከል በቂ እንቅልፍ ሳያገኝ በቀጥታ ወደ ዝግጅቱ አዳራሽ የሚገባበትም አጋጣሚ የበዛ ነበር። ይሁን እንጂ ታማኝ አንድም የድካም ስሜት ሳይታይበት በተገኘበት ዝግጅት ላይ ሁሉ ለሶስት ወራት በጉጉት ሲጠብቀው የነበረውን ኢትዮጵያዊ አስደስቷል።
ወደ ሜልበርን ዝግጅቱ ስንመለስ ታማኝ ወደ አውስትራሊያ ይመጣል ከተባለበት ቅጽበት ጀምሮ በጉጉት ሲጠብቅ የነበረው የሜልበርን ኢትዮጵያዊ በድንገተኛ የበረራ መሰረዝ ምክንያት በዝግጅቱ እለት ሊደርስ ያለመቻሉ ሲነገረው መበሳጨቱ አልቀረም።
ይሁናና ታማኝ በመካከሉ መገኘቱ ብቻ ያስደሰተው የሜልበርን ኢትዮጵያዊ የዝግጅቱን ለሳምንት መተላለፍ በጸጋ ተቀብሎ ቆይቷል።
አይደርሱ የለምና በጉጉት ይጠበቅ የነበረው ቀን ደረሰ። የሜልበርን ኢትዮጵያዊም ወደ ዝግጅቱ አዳራሽ ይጎርፍ ጀመር። አርቲስት ታማኝ ወደ ዝግጅቱ አዳራሽ ከመድረሱ አንድ ሰአት በፊት አዳራሹ በሰው ተጨናነቀ። ወንበር በፍለጋም ጠፋ።እስከ 350 ሰው እንደሚይዝ የሚታወቀው አዳራሽ ተጨማሪ 100 ወይም 150 ሰው ለማስተናገድ ተገደደ።
በመጨረሻም በጉጉት የሚጠበቀው ታማኝ በየነ አዳራሹ አካባቢ እንደደረሰ ሲሰማ፤ አዳራሹ ውስጥ የነበሩ እናቶች እህቶች ወንድሞቻና ሕጻናት አዳራሹን ለቀው በመውጣት

አምባው ጃልዬ!!
ጀግናው ልጅሽ ታማኝ መጣልሽ ታማኝ ምን አለ አገሬን ለሰው አልሰጥም አለ! ታማኝ የታለ .....
በሚሉ ዜማዎች በታጀበ አቧራ ያስነሳ ደማቅ ጭፈራ ተቀበለው። ጭፈራው ታማኝ አዳራሹ ውስጥ ገብቶ በግራ ቀኝ ያለውን ታዳሚ ሰላምታ እየሰጠ ከተዘጋጀለት የክብር ስፍራ እስኪደርስ አልቆመም። ሙሉው ቪዲዮ ኤዲት ተደርጎ እስኪወጣ ይህን ጥቂት ደቂቃ የሚያሳይ ክሊፕ ይመልከቱ
ባጠቃላይ በሜልበርን የተደረገለት አቀባበል በብዙዎች ግምት በደቡብ አፍሪካ ከተደረገለት አቀባበል የሚሰተካከል አልያም የሚበልጥ ኢትዮጵያዊው ለአርቲስት ታማኝ ያለውን ፍቅርና ክብር የገለጸበት ነበር።(ሙሉ ቪዲዮው በቅርቡ ለእይታ ይበቃል)
ታማኝ የክብር ቦታውን እንደያዘ የዝግጅቱ አስተባባሪ ግብር ኅይል ሊቀመንበር የሆኑት አቶ ሳምሶን አስፋው አጠር ያለ የእንኳን ደህና መጣህ ንግግር ካደረጉ በኋላ አርቲስት ታማኝን ወደ መድረክ ጋበዙ።
ታማኝ ዝግጅቱንን የጀመረው በግፍ ለሞቱት ወገኖቻችን የአንድ ደቂቃ የህሊና ጸሎት በማድረግ ነበር።
page2image17464
ፊሽካ ተነፋ ዝግጅቱ ተጀመረ። ታማኝም መድረኩን ተቆጣጠረ ፤ ከጡጦ ቀጥሎ የጨበጥኩት ማይክራፎን ነው በማለት ከጅምሩ ታዳሚውን በሳቅ ያንከተከተው ታማኝ ይህን አብሮ አደግ ሙያውን ችላ ብሎ ወደ አክቲቪስትነት ሊገባ የተገደደው በሃገርና በህዝባችን ላይ እየደረሰ ያለው ለከት ያጣ የመብት ረገጣ በፈጠረበት ቁጭት መሆኑን እያዋዛ ማስረዳቱ ቀጠለ።
ከራሱ ሕይወት በመነሳት በግራ ቀኝም የሃገራችንን ወቅታዊና ነባራዊ ሁኔታዎች እያሰባጠረ በሚገርም መልክ መሳጭ መልዕክቶችን በማስረጃ እያስደገፈ አቀረበ።
እንዲህ እንዲህ እያለ ለአንድ ሰአት ከዘለቀ በሗላ ወደ ዋናው የገቢ ማሰባሰቢያ የጨረታ ፕሮግራም ተሸጋገረ። ለጨረታ የቀረበው የታዋቂው ሰዓሊ ታምራት ገብረማሪያም “ያልታወቀው ጀግና” የሚል ስያሚ ያለው የቅብ ስራ ሲሆን ሰአሊ ስዕሉ ነው።
መነሻው 500 ብር ሆኖ ጨረታው ተጀመረ። በሚያስገርም ርብርብ 20 ደቂቃ ሳይሞላ 10 ሺህ ዶላር ደረሰ ። ቀዝቀዝ ሲል ሙቀት እየፈጠረ በአጭሩ እንዳይቀጭ እድሜውን እያራዘመ ተጉዞ በመጨረሻም የላሊበላ ሬስቶራንት ባለቤት አቶ አበራ 30 ሺህ ዶላር ላይ አሸናፊ ሆነዋል።ጨረታውን ያሸነፉት አቶ አበራ ያሸነፉትን የቅብ ስእል መልሰው በልጃቸው አበርካችነት ለታማኝ በስጦታ መልክ ሰጥተዋል። በተለይ መጨረሻ ላይ በላሊበላ ሬስቶራንት ባለቤት በአቶ አበራና በፉትስክሬይ የሚገኘው አቢ ኮስሞቲክስ ባልቤት በአቶ መስፍን መካከል ጨረታውን ለማሸነፍ የነበረው ፉክክር የዝግጅቱን ታዳሚ ያስደነቀ ነበር።
በዚህ አጋጣሚ ለዚህ ዝግጅት መሳካት ከአስተባባሪው ኮሚቴ ጋር በመሆን ልዩ ልዩ እገዛና ትብብሮችን ለአደረጉ ወገኖች ተገቢው ምስጋና በቀረበበት በአዘጋጁ ኮሜቴ ሰብሳቢ የመግቢያ ንግግር ላይ በተፈጠረ ስህተት ከፍተኛ ትብብር ሲያደርጉ የነበሩት የአቢ ኮስሞቲክ ባለቤት አቶ መስፍን ስይጠቀሱ በማለፋቸው አዘጋጅ ኮሚቴው ከፍ ያለ ይቅርታ እየጠየቀ እንሆ በኢሳት ደጋፊዎች ስም አቶ መስፍንን ላደረጉት ትብብር ከፍተኛ ምስጋና ያቀርባል።
ወደ ዕለቱ ዝግጅት ስንመለስ። ጨረታው በአቶ አበራ አሸናፊነት ተጠናቀቀ። ሜልበርን ሬከርዱን በመስበር ታሪክ ሰራ። ይህ ሪፖርት በተጻፈበት ወቅት ከወጭ ቀሪ ሂሳቡ ባይሰላም በእለቱበጨረታ የተገኘው ገቢ በትኬትና በልዩ ልዩ ሽያጮች ከተገኘው ገቢ ጋር ተዳምሮ ባጠቃላይ 50 ዶላር በላይ ገቢ መገኘቱ ታውቋል ።
በውጤቱ የተደሰተው ታማኝ ጨረታውን እንደዘጋ የገባው ወደ ጭፈራ ነበር። ጥቂት ደቂቃ የያዙ የቪዲዮ ክሊፖችን ይመልከቱ በኦርጋኒስቱ ዳንኤልና በጊታሪስቱ ጆሲ በመታጀብ የብሄረሰብ ዘፈኖን በመጫወት ታዳሚውን ኢትዮጵያዊ አስደስቷል። በዚህ አጋጣሚ ለኦርጋኒስቱ ዳንኤልና ለጊታሪስቱ ጆሲ ለዝግጅቱ ማማር ያለክፍያ በሰጡት ግልጋሎት አዘጋጅ ኮሚቴው በኢሳት ስም ልባዊ ምስጋና ያቀርባል።
አሁንም ወደ መድረኩ ስንመለስ ታማኝ ታዳሚውን በሙዚቃ ካዝናና በሁላ በዚህ ዝግጅት የተገኘውን ኢትዮጵያዊ አመስግኖ ዝግጅቱ ከመጠናቀቁ በፊት ከቪክቶሪያ የኢትዮኦጵያ ኮሚኒቲ ለታማኝ የተበረከተውን የማስታወሻ ስጦታ ከሊቀመንበሩ ከአቶ ጋሻው አንለይ እጅ ተቀብሏል።
በዚሁ ዝግጅት ፍሬው ተስፋዬ ገነት ሃብተ ወልድና ጌጤ በየመሃሉ የስነ ግጥም ስራዎቻቸውን በንባብ አቅርበዋል።
በመጨረሻም ዝግጅቱ መጠናቀቁ ተገልጾ ታዳሚው ተሰናብቷል።
page3image19744
የሜልበሩን ዝግጅት በአስደሳች መልክ ተጠናቀቀ ። የታማኝ የአውስትራሊያ ቆይታ ግን ሌላ አንድ ዝግጅት ይቀረዋል። የሜልበርን ዝግጅት ከተደረገ ከሁለት ቀን በኋላ ወደ ወደ ፐርዝ በመብረር እሮብ በበፐርዝ ዝግጅት ተገኝቶ 14 ሺህ ዶላር ማሰባሰብ ችሏል። የፐርዝ ዝግጅትን ሪፖርት እዚህ ላይ ያንብቡ
አርቲስት ታማኝ በፐርዝ ዝግጅት የአውስትራሊያውን ጠቅላላ ዝግጅት አጠናቆ ሃሙስ ወደ ሜልበርን ተመለሰ። ሁለት ቀን በሜልበርን ቆይታ አድርጎ ቅዳሜ ኦገስት 25 ቀን ወደ ኒውዚላን ኦክላንድ በመብረር የመጨረሻውን የኦሽንያ ዝግጅት እሁድ ኦገስት 26 በኦክላንድ አድርጓል፡፤ በዚህም ዝግጅት በኒውዝላን ዶላር 24 ሺህ (በአሜሪካ 18 ዶላር) ማሰባሰብ መቻሉና የኦክላንድ ዝግጅት ከሜልበርን ቀጥሎ በህዝብ ብዛትም ሆነ በተገኘው ገንዘብ መጠን በሁለተኛ ደረጃ የደመቀ ዝግጅት እንደነበርም ታውቋል። የኦክላንድን ዝግጅት ሪፖርት እንሆ
የኦክላንዱን ዝግጅት አጠናቆ በማግስቱ ወደ ሜልበርን የተመለሰው አርቲስት ታማኝ በተመለሰበት ዕለት ሰኞ በሜልበርን ኢትዮጵያዊ የክብር እራት ግብዣ ተደርጎለት ስጦታም ተበርክቶለታል። በ እራት ግብዣው የተገኙት ኢትዮጵያዊያን በተለይ ይህን ያህል ግዜ ተለይቷቸው ከኛ ጋር እንዲቆይ ለፈቀዱት ለታማኝ ቤተሰቦች ከፍ ያለ ምስጋና አቅርቧል።
በማግዝቱ ማክሰኞም አዘጋጅ ኮሚቴው አባላት የባርብኪው ግብዣ አድርገውለት ዕሮብ ቀን ወደ አሜሪካ ተሸኝቷል።በ 9 ከቤቱ የወጣው ታማኝ ወደ ቤተሰቡ የደርሰው ከ 21 ቀናት በኋላ መሆኑነው። በነዚህ 21 ቀናት ቆይታው በጠቅላላው 64 ሰአታት የሚሸፍኑ 11 ተከታታይና አድካሚ በረራዎችን አድርጓል። የአላማ ጽናቱ ጉልበትና ብርታት ሆኖት እንጂ በአውስትራሊያ ያደረገው ቆይታና ያሳለፈው ግዜ እጅግ አድካሚ እንቅልፍ አልባና ጉዞውም አሰልቺ ነበር። በዚህ አጋጣሚ የዥግጅቱ አሰተባባሪ ኮሚቴ ለአርቲስት ታማኝና ለቤተሰቡ ከፍ ያለ ምስጋና እያቀረበ ፤ ለዝግጅቱ መሳካት ከኮሜቴው ጎን ለቆመው ለሜልበርን ኢትዮጵያዊ ሁሉ አኩርታችሁናልና ክብር ለናንተ ይሁን እንላለን።
ሜልበርን ኦገስት 2012 

No comments:

Post a Comment