(ተመስገን ደሳለኝ፣ “ከመለስ በሁዋላስ?” በሚል ርእስ ካቀረበው ፅሁፍ የመጨረሻው አንቀፅ)
ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ምን አልባት ድፍረቱካላቸው ከህወሓት እና ብአዴን ‹‹የስልጣን እገታ›› ወደአርነት የሚመሩ የፖለቲካ መንገድ ማግኘት ላይቸገሩይችላሉ፡፡ ለምሳሌ በዋናነት የአጋቾቹ ጉልበትበሰራዊቱ እና በደህንነት ላይ የተመሰረተ መሆኑንአጢነው ‹‹የጠቅላይ ሚኒስቴር መንበራቸው››ንስልታዊ ሆነው መጠቀም ከቻሉ ወንዙን ለመሻገርአይቸገሩም፡፡ በአናቱም አቶ መለስ ደህንነቱን እናሰራዊቱን ሙሉ በሙሉ በግላቸው ከመቆጣጠራቸውበፊት (ከ1983ዓ.ም. -1993 ዓ.ም.) የ‹‹ጉልበተኛ ጓደኞቻቸውን አቅም››ያፍረከረኩት መንግሥታዊ ስልጣናቸውን በመጠቀም በመሆኑ ከእሳቸው ስልት(ከመለስ አጠገብ ሆኜ ብዙ ተምሬአለሁ እንደሚለት) ትምህርት ወስደው ከሆነለብልህነታቸው እና ለአርቆ አሳቢነታቸው አድናቆት አለኝ፡፡
እንዲሁም ሕገ-መንግሥቱን በሚገባ ለመተግበር ከቆረጡም በራሱ በህገ-መንግስቱ ጡንቻቸው ከተገዳዳሪዎቻቸው ሊበረታ የሚችልበትን ዕድልአያጡም፡፡ ይኸውም በህገ መንግሥቱ ‹‹የመከላከያ መርሆች›› በሚልበአንቀጽ 87፣ በቁጥር 1 ላይ፡- ‹‹የሀገሪቱ የመከላከያ ሠራዊት የብሔሮችየብሔረሰቦች እና የህዝቦችን ሚዛናዊ ተፅዕኖ__ ያካተተ ይሆናል›› የሚለውንሊጠቀሙበት ይችላሉ፡፡ እናም ይህ አንቀጽ ይከበር ዘንድ ሠራዊቱ የብሔርተዋፅኦን እንዲጠበቅ ‹‹የመዋቅር ማስተካከያ›› ካደረጉ ከሕገ-መንግሥቱይልቅ ለፓርቲ ታማኝ በሆነው ሠራዊት ላይ ድንገት ደርሰው የሀይል ሚዛኑንማመጣጠን አይከብዳቸውም፡፡ ይህን ለማድረግ ደግሞ የተጠቀሰውየህገ-መንግሥቱ አንቀፅም ድጋፍ ይሰጣቸዋል፡፡
እንዲሁም ሕገ-መንግሥቱን በሚገባ ለመተግበር ከቆረጡም በራሱ በህገ-መንግስቱ ጡንቻቸው ከተገዳዳሪዎቻቸው ሊበረታ የሚችልበትን ዕድልአያጡም፡፡ ይኸውም በህገ መንግሥቱ ‹‹የመከላከያ መርሆች›› በሚልበአንቀጽ 87፣ በቁጥር 1 ላይ፡- ‹‹የሀገሪቱ የመከላከያ ሠራዊት የብሔሮችየብሔረሰቦች እና የህዝቦችን ሚዛናዊ ተፅዕኖ__ ያካተተ ይሆናል›› የሚለውንሊጠቀሙበት ይችላሉ፡፡ እናም ይህ አንቀጽ ይከበር ዘንድ ሠራዊቱ የብሔርተዋፅኦን እንዲጠበቅ ‹‹የመዋቅር ማስተካከያ›› ካደረጉ ከሕገ-መንግሥቱይልቅ ለፓርቲ ታማኝ በሆነው ሠራዊት ላይ ድንገት ደርሰው የሀይል ሚዛኑንማመጣጠን አይከብዳቸውም፡፡ ይህን ለማድረግ ደግሞ የተጠቀሰውየህገ-መንግሥቱ አንቀፅም ድጋፍ ይሰጣቸዋል፡፡
በእርግጥ ይህንን ማድረግ ‹‹ራስንም ማደን›› መሆኑ የሚገባን አቶ መለስህይወታቸው ካለፈ በኋላ እና ተተኪያቸው ከመመረጡ በፊት በእሽቅድምድምለ34 ኮሎኔሎች የተሠጠውን የብርጋዴል ጄኔራልነት ማዕረግ ከህጋዊነቱ አንፃርስናየው ነው፡፡ ምክንያቱም ህገ-መንግሥቱ የጄኔራል ማዕረግ በምን መልኩሊሰጥ እንደሚገባው ይደነግጋል፡፡ ‹‹የፕሬዘዳንቱ ሥልጣንና ተግባር››በሚለው ክፍል አንቀጽ 71 ቁጥር 6 ላይ እንዲህ ይላል፡- ‹‹በጠቅላይ ሚኒስትሩአቅራቢነት በህግ በተወሰነው መሠረት ከፍተኛ የውትድርና ማዕረጎችንይሰጣል›› ኃይለማርያም ሊያነሱት የሚችሉት ጥያቄም ‹‹የ34ቱ ጄኔራሎችሹመት በማን አቅራቢነት የተካሄደ ነው?›› የሚል ይሆናል፡፡ ሆኖም ጠቅላይሚንስትሩ የሚጠበቅባቸው ጥያቄ ማንሳት ብቻ ሳይሆን ከሹመቱ አንድምታተነስተው በሰራዊቱ ለመጠቀም የሚሞክረው ኃይል ምን ያህል ደፋር እንደሆነመረዳትም ይኖርባቸዋል፡፡ (በነገራችን ላይ ይህን ሹመት በህወሓት እናበብአዴን መካከል ተከሰተ ከተባለው ከስልጣን ፉክክር ጋር የሚያያይዙትየፖለቲካ ተንታኞች አሉ) ሌላው ኃይለማርያም ስልጣናቸውን ከዕገታ ነፃሊያወጡ የሚችሉበት አማራጭ ከፓርቲው ይልቅ (በይበልጥ) መንግሥታዊስርዓቱን በመጠቀም ሊሆን ይችላል፡፡ እንደሚታወቀው የኢትዮጵያ ማዕከላዊመንግሥት እጅግ ጠንካራ እና ሚሊተራይዝድ ሆኖ የተዋቀረ ነው፡፡ ይህንየሚያውቅ መሪ ደግሞ ከላይ እስከ ቀበሌ ድረስ ማዘዝ የሚቻልበትን ልማድበሚገባ ይተገብራል፡፡ ይህን ዓይነቱን መንግሥታዊ መዋቅር የወረሱት አቶመለስም በ1993ቱ ክፍፍል ወቅት ተገዳዳሪዎቻቸው በፓርቲ ህገ-ደንቦችአጥረው ሊያቆሟቸው ሲሞክሩ እርሳቸው ግን ይህን ተሻግረው መንግስታዊመዋቅሩን በመጠቀም (ለስዬ ፍርድ ቤትን እንደተጠቀሙት) የሃይልትንቅንቁን ተሻግረዋል። ኃይለማርያምም ይህን ሊያደርጉ የሚችሉበት ዕድልሊኖር ይችላል፡፡ እርግጥ ነው ይህን ማድረግ የሚችሉት ጥቂት ዓመታትሀገሪቷን መምራት ሲችሉ ብቻ ነው፡፡ በእንዲህ አይነት ሁኔታ ወንዙን መሻገርከቻሉ ደግሞ ገላጣው ሜዳ ላይ ይደርሳሉ፡፡ ተጨማሪ የመለስን ስልትምያገኛሉ፡፡ መለስ ከዚህ በፊት የውስጣዊ ኃይል መደላደላቸውን ከፓርቲ ፓርቲሲቀያይሩ ሚሊተሪውን እና ደህንነቱንም እንዲሁ እያፈራረቁ የተጠቀሙበትንማለቴ ነው፡፡
በአናቱም ሊጫኗቸው የሚሞክሩትንም እንዲሁ መለስ እንዳደረጉት‹‹ግራ-ዘመም ጠባብ ብሄርተኞች ናቸው›› የምትል ካርድ ለምዕራባውያኑማሳየት ይችላሉ (ምዕራባውያኑ ኃይለማርያምን Pragmatic፣ ነባሮቹን ደግሞማቻቻል የማያውቁ ከሚሉት አንፃር) እንግዲህ መጪዎቹ ጊዜያቶችለኃይለማርያምም ሆነ ለነባር ታጋዮቹ ፈታኝ ይሆናሉ ብሎ መገምትአያስቸግርም፡፡ ከምንም በላይ እንዲህ ዘግይቶም ቢሆን ኢህአዴግ የእኛንየዜጎቹን ድምፅ መስማት ቢጀምር እጅግ የተሻለ እንደሆነም ማስታወስያሻል፡፡
No comments:
Post a Comment