Wednesday, October 17, 2012

ዜና በጨዋታ፤ የኢቲቪው ጋዜጠኛ “ፕሮፖጋንዳ በቃኝ” ብሎ “ነካው!”


አቤ ቶኪቻው
ሰለሞን መንግስት ይባላል። በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ውስጥ የእንግሊዘኛው ክፍል ባልደረባ ነው። ዛሬ በፌስ ቡክ ግድድዳው ላይ “I have said “enough is enough“ and decided to never be back in that dirty propaganda factory called ERTA.”  የሚል ለጥፎ አስነብቦናል።ዜና በጨዋታ፤ የኢቲቪው ጋዜጠኛ “ፕሮፖጋንዳ በቃኝ” ብሎ “ነካው!”
መቼም ሰው ከኢትዮጵያ ቴሌቪዥን “በቃኝ ብያለሁ በቃኝ” ብሎ ቢማረር ምን ሆኖ ነው? ተብሎ አይጠየቅም። ምክንያቱም ቤቱ ኢቲቪ ነው!
ይልቅስ በኢቲቪ አሁን ድረስ እየሰሩ ያሉ ወዳጆቻችን ምን ሆነው ነው የማይለቁት? ኢቲቪው ላይ ምነው ወይዘሮ አዜብ ሆኑበት? የሚለው ጥያቄ መልሱ ግር ይላል።
በነገራችን ላይ አንድ ወደጄ ነው ይቺን አዲስ ፈሊጥ የነገረኝ። አንድ ሰው የሆነ ቦታ ገብቶ አልወጣ ካለ “ምነው አዜብ መስፍንን ሆንክ!?” እያሉ መጠየቅ በከተማው ተለምዷል አሉ። ይሄ ያነጋገር ፈሊጥ መፀዳጃ ቤት ገብቶ አልወጣ ላለ ሰው፣ ከመኝታው አልነሳ ላለ እንቅልፋም ሁሉ አገልግሎት ላይ ይውላል።
አሁንም በነገራችን ላይ ወሮ አዜብ በወሮ ሚሚ በኩል “ቤተመንግስት ይሄን ያክል ብርቅ ነው እንዴ! ቀስ ብዬ ወጣለኋ ሀዘኑ ይብረድልኝ እንጂ!” የሚል መልዕክት አስተላልፈዋል አሉ! “ወይ ጉድ ለእነዚህ ወሮዎች እና ለአንዳንድ ወሮበሎች የሚሆን መድሃኒት ጠፋ አይደል!?” አሉ አይደል በሆድዎ…? ተነቃቅተናል!
የሆነው ሆኖ ከኢቲቪ ላይ እስካሁን አዜብ መስፍን የሆኑበት ጋዜጠኞች እስካሁን ያለመልቀቃቸው ምስጢር ለስብሰባ ውጪ ሀገር ስላልተላኩ ነው እንጂ እንኳን ሌላ ሃይለራጉኤልም ለቋል። የምር ግን ጋዜጠኛ ሃይለራጉኤል እና ባለቤቱ ሂሩትን የበላች አሜሪካ አልጮህ አለችሳ…!
ለማንኛውም ሰለሞን መንግስት ዛሬ በፌስ ቡክ ግድግዳው በለጠፈው መሰረት በቃኝ ብሎ ከኢቲቪ ወጥቷል። በርካቶችም ልክ ከአንዳች ህመም ተፈወስኩ ያል እስኪመስል ድረስ “የእንኳን ደስ አለህ” መልዕክት እና “እሰይ የኔ አንበሳ” የሚል ማበረታቻ  አጎድጉደውለታል። ጋዜጠኛው በውስጥ መስመር እንዳወራኝ  እሁድ ጥቅምት አራት ለስራ በተላከበት ሀገር ነው የኢቲቪ ስራ “ሴራ” ነው ብሎ የነካው።
“ነካው”… ቃሉ የአራዳ ሲሆን “ሄደ” “አመለጠ” “ኮበለለ” የሚለውን ትርጓሜ ይይዛል!

No comments:

Post a Comment