ለዘመናት ሁለንተናዊ ከብሩዋን በህዝቦች መተሳሰብ እና አበሮ የመኖር ባሀል አዳብራ በአበው ተጠብቃ ለዘመኑ ከፈፍልሀ ገዛ የበቃች አገራችን ወዴት እያመራች ነው ይምለወን ሳስብ በእውንት እንቅልፍ ይነሳል። ለነገሩ ቡዙዎች በግፍ በመከራ እየተስቃዩ ባሉበት በዚህ ዘመን ለትተኛ ያምርህ ነበር አትሉኘም ? መልሳችሁ እንደው ማሰብህ !! እንደምሆን እርግጠኛ ነኝ።
ትላንት በባርነት ቀንብር ሲዳከሩ ፣በባእዳን እጅ በገዛ አገራቸው አሳር ሲቆጥሩ የኖሩ ብዙ ህዝቦች እና ሀገራት የሃይማኖት ነጻንታቸውን ፣የመናገር መብታቸውን ፣ በንጻነት በገዛ ሀገራቸው የምንቀሳቀስ መብታቸውን ፣ ህዝቦች በሀገራቸው የትኛውም ከፍል ሀብት ነብረት አፈርተው የመኖር መብታቸወን ፣ወዘተ አስከብረው እየኖሩ ባሉበት በዚህ ዘመን ፣ጥንታዊ ታሪክ ያላት፣ አይበገሬ የኢትዮጵያ ሕዝብ በዝህ ሁኔታ ነፍጥ መከታ ባርጉ የዘመኑ ዘረኞች ከላይ የተዘረዘሩ እና ለሎችን መብቶች ተነፍጎ ማየት መንኛ ዘግናኝ የታሪክ አዝቀት መሆኑን መገመት አያቅትም ።
ዛሬ ኢትዮጵያዊ ነኝ ባይ ሁሉ እራሱን መፈትሽ ያለበት ወቅት ነው ። አገረ በመከራዋ ጊዜ ያልደረሱላት ነጌ የቁርጥ ቀን ልጆች ታግለው አንገቱዋን የደፋች ኢትዮጵያ የሁሉ መኖሪያ ሲያደርጉዋት ሀፍረታችን መሽከም የከብዳቸዋል ። ስለዝሀም ሁሉመ በሚችለው መንገድ ለዛሬዋ ኢትዮጵያ አለሁለሽ አይዞሽ በማለት የበኩሉን መወጣት የገባዋል ። የዘረ ፣የሃይማኖት ፣ የፖለቲካ ድርጅቶች አምልኮን በመተው የነገዋ ኢትዮጵያ ፣ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ዴሞክራሲያዊና ሰብአዊ መብቱ የተከበረበት፣ የኢኮኖሚ ብልፅግናና ማኅባራዊ ፍትህ የሚያገኙበት፣ የዜጎች ህይወት፣ ደህንነትና ጥቅም የተከበረበት ሃገር እንድትሆን ለማደርግ በሚረዳ አመለካከት ተስባስቦ በጋራ መስራት የገባዋል ።
ፍቅሬ አናራ
No comments:
Post a Comment