Wednesday, January 25, 2012

የወያኔ መርበትበት ለነገው ተስፋ ፣ ወጣቱ እያደረገ ላለው ትግል ጥንካሬ ነውና የተቀናጀ ድጋፍ ያሻል!!


ኢትዮጵያ ሀገራችን ባሳለፈቻቸው ዘመናት ለገጠሙዋት ለውስጥና ለውጭ ጠላቶች ወጣት ልጆቿ ከቀደሟቸው አበው እና እማው በወረሱት ኢትዮጵያዊ ጀግነት ሀገርንና ሀገራዊ እሴት ሲያስጠብቁ መኖራችው እሙን ነው ፡፡
ሀገራችን ካጋጠሙዋት የወስጥና የውጭ ጠላቶች ሁሉ እንደ ወያኔ የህዝቡዋን የአንድነት መንፈስ ያናጋ የሀገሪቱን ህልውና አደጋ ላይ የጣለና የህዝብ ወገን በመምሰል ሀገሪቱን እያስተዳደረ የህዝብ ሀብት የዘረፈ (እየዘረፈ ያለ) ተጠቃሽ የህዝብ ጠላት ያለ አይመስለኝም ፡፡
ዛሬ ወጣቱ ላለፉት 20 አመታት ሲስማው የኖረው የውሽት ፖለቲካ መታገስ ከሚችለው ባለይ ያማረረው እኔ አውቅልሃለው የሚለው የመለስ እና አንጃዎቹ ንቀት እና አንባገነንነት የነገ ህልውናውን ጥያቄ ውስጥ ማስገባቱ እንዲሁም በሀገሪቱ የተንሰራፉት ኢፍትሀዊ አስተዳደር የወለዳችው ችግሮች ወጣቱን ትውልድ የለውጥ ፈላጊነትን ስሜት ፈንቅሎ ማነሳሳቱን ከራሴ እርቄ ሌላ ምስክር መጥራት የሚያሻ አይመስለንኝም፡፡


በአሁኑ ሰአት ያለው የወያኔ ሥርዓት በሀገሪቱ አቻ በሌለው ሁኔታ በሚያራምደው የጎሳ ፖለቲካውና ይህንን ለመተግበር እስከ ቀበሌ ባወረደው ድርጅታዊ መዋቅር በሕዝቡ ውስጥ ትልቅ እርስ በርስ መፈራራትን በማንገስ በስልጣን ላይ ለመቆየት የሚያደርገው መሯሯጥ ለዲሞክራሲ ልፍትህና ለአንድነት የቆሙትን ኃይሎች የሚከፍሉትን መስዋትነት ከፍ እንዲል ሊያደርገው ይችል እንደሆን እንጅ ከቶ ሊያቆመው እንደማይችል ወያኔም ጭምር ያውቀዋል።
እስከ ዛሬ ድረስ በተለያዩ ኢትዮጵያዊያንና የአለም አቀፍ ሰባዊ መብት ድርጅቶች እንዲሁም ኢትዮጵያዊያን የፖለቲካ ድርጅቶች ነጋ ጠባ ሲያነሱት የቆዩት እንደ ጋምቤላ የአኝዋክ የጅምላ ፍጅት እና መሰል ግድያዎች ወንጀል የሚጠየቁት  ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊም  መሆናቸውን ዛሬ ከራሳችው ከጋምቤላ ክልል ፕሬዘዳንት Omod Obang Olum የግምገማ ውጤት ሲሰማ የሰውየው የሀገር አጥፊነት ለመረዳት  ለዘገዩ ኢትዮጵያዊያን ምናልባት ከቡዙ ትንሿ መረጃ ሊሆን ይችላል፡፡
የወያኔ መለስ አገዛዝ ተማሪው ዛሬ ዩኒቨርስቲ በመግባት የእለት ተእለት ስራው የሆነወን ትምህርቱን ጥራቱ በጠበቀ መልኩ ተምሮ የነገ ሀገር መሪነቱን ድርሻ
መወጣት የሚችለበት መንም ዋስተና በሌለበት መልኩ በተደራጁ ዩኒቨርስቲዎች ውስጥ ተማሪዎችን አጉሮ ከማሰቃየቱም አልፎ ተማሪውን በደቡብ፣ በትግርኛ በኦሮሚኛና በአማርኛ ተናጋሪነት በጎራ በማደራጀት እንደ ባቢሎን ግንብ ዘመን መርገም የኢህአዴግ ደጋፊ የሆኑ እንኳን ሳይቀሩ እርሰ በራስ እንዳይደማመጡ እና እንዳይተማመኑ እያደረገ ቢሆንም ተማሪው የለውጥ ፈላጊነቱን በተለያየ መንገድ እየገለጸ ይገኛል፡፡ ለዝህም በቅርቡ በዓለም አቀፍ እስላማዊ ድርጅት ይተዳደር የነበረው የአወሊያ ትምህርት ቤት በወሎ  ዩኒቨርስቲ በወለጋ ዩኒቨርስቲ   በአዳማ ዩኒቨርስቲ    ባለፈው የትመህርት ዘመን መጀምሪያ ላይ አርባ ምንጭ ዩኒቨርስቲ እና በለሎች የትመህርተ ተቋሞች በተናጠል በሚመስል መልኩ እየተደርጉ ያሉት መነሳሳቶች ለትግሉ ስር መስደድ ማረጋገጫ ናቸው፡፡

እንደ እኔ ገዥው ወያኔ ከላይ ለመጥቀስ እንደሞከርኩት ተማሪውን በዘር በቁዋንቋ በሀይማኖት ከፋፈሎ የጋራ በሆነችው የሀገራችን ጉዳይ እንዳይነጋገሩና እርስ በርስ መተማመን እንዳይኖረው ተግቶ እየሰራ በመሆኑ የተማሪው የለውጥ እንቅስቃሴ መሪነት ሚና እንደ ከዝህ በፊቱ በጉልህ እንዳይጫወት ማነቆ ሆኖበታል፡፡
ከተለያዩ አካባቢ ወደየ ተምህርት ተቛማት የገቡ ተማሪዎች ከሚማሩበት አካባቢ ማህበርሰብ ጋር ያላቸውን ግንጙነት ከአካባቢው ተመልምለው በገቡ ተማሪ መሰል ካድሬዎች እንቅስቃሴ የተገደበ መሆኑ ሌላው የህዝብ እና ተማሪዎች መረጃ ልውውጥ አንዱ ማነቆ ነው፡፡
መለስ እና ገብረ አበሮቹ እንደተለመደው የተማሪ አመጽ በማፈን የኢትዮጵያን ህዝብ ምሬት እና ለለውጥ ተነስቶ በቃ እያለ ያለበትን ሁኔታ የሚያስቆም መስሎት በቅጀት እየደነበረ ባለበት በዝህ ሰአት የማያዳግም የተባበር ክንድ መስንዘር የኛ የኢትዮጵያዊያን ድርሻ ነው.. ለዝህም በሀገርና ከአገር ውጪ ያለን ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን የመለስን የመከፋፈል ሴራ ወደ ጎን ትተን ሀላፊነት የተሞላበት ርብርቦሽ ለምናልማት የሁላችን የነገዋ ኢትዮጵያ ግንባታ ታላቅ ቦታ አለው፡፡
ወጣቱ በህዝቡ ስር እያደርገ ያለውን እንቅስቃሴ ከወትሮ በበልጠ በመረጃ ልውውጥና እስከ አሁን የሚደርገውን የትግል ዘይቤ በተቀናጀ አቅጣጫ በማስኬድ ወያኔ የሚሄድበትን ጎጠኛ አካሔድ መስበር የሚቻል መሆኑን ከሰሞኑ ውያኔ ካሳየው መርበትበት እና በየክልሉ እያደረገ ካለው ግምገማ መረዳት አያዳግትም፡፡
ስለዚህም የዚህን ህዝብ ገዳይ እና አገር አጥፊ በጋራ በቃ እንበለው!!!

Fikre Anara  
19.01.2012
Oslo

No comments:

Post a Comment