Thursday, August 2, 2012

ሬዲዮ ፋና ጠቅላይ ሚኒስትሩን ማን ሊተካቸው እንደሚችል ከአድማጮቹ ጋር ተወያየ


አውራምባ ታይምስ (አዲስ አበባ) – የገዢው ፓርቲ ልሳን የሆነው ፋና ብሮድካሲቲንግ ኮርፖሬሽን በትናንትናው ስርጭቱ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማይኖሩበት ጊዜ ማን ሊተካቸው እንደሚችል በቀጥታ ስርጭቱ የህግ ባለሙያዎችን ጋብዞ አወያየ፡፡
የሬዲዮ ፋና ዋና ጽ/ቤት


ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በህይወት የሉም በሚባልበት በአሁኑ ወቅት፣ ሬዲዮ ጣቢያው በዚህ ርዕሰ ጉዳይ ዙሪያ ህዝብን ለማወያየት መነሳቱ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በህይወት ባይኖሩ ነው የሚለውን ያረጋግጣል ሲሉ አስተያየት ሰጪዎች ግምታቸውን ይሰጣሉ፡፡ በሬዲዮ ጣቢያው የተጋበዙ የህግ ባለሙያዎች አቶ መለስ በማይኖሩበት ጊዜ ም/ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደሚተኳቸው የሚጠቁም አስተያየት ሲሰጡ ተደምጠዋል፡፡

No comments:

Post a Comment