Saturday, August 18, 2012

ሳቃችሁ ናፈቀኝ !! በእንግዳ ታደሰ


እባክህ ጌታዬ ይህን ሰው ገላግለኝ
page1image1640
ቁልፉን በእጁ ይዞ ከፍቶ አልስገባ አለኝ ፡፡ ነጋድራስ ተሰማ እሸቴ

የቀድሞው የ- ኢህዴን መሥራች አቶ ያሬድ ጥበቡ ሰሞኑን ለአውራምባ ታይምስ ድረገጽ ጋዜጣ አዘጋጅ ለአቶ ዳዊት ከበደ በጠቅላይ ሚንስቴር መለሰ ዜናዊ የጤና ዙርያ የሰጡትን ቃለ መጠይቅ በአንክሮ ካዳመጡት መሃል አንዱ ነኝ ፡፡ አቶ ያሬድ በዚህ የጠቅላይ ሚንስትሩ ጤና ዜና ዙርያ እየተሰሙ ያሉትን የተለያዩ ያለየላቸውን ዜናዎች ፈርጠም ብለው እይታቸውን ለማስረገጥ ያደረጉትን ሃሳባቸውን አልቃወምም ፡፡መብታቸውም ነዉና ፡፡
ከአቶ ያሬድ ጥበቡ ቃለ መጠይቅ ጋር በአጠቃላይ ባይሆንም ፣ በአንዳንድ ሃሳቦች ላይ ልዩነቴን ለማሳየት የማደርገውን ሃሳቤን አቶ ያሬድ በክፉ ዓይን እንደማይመለከቱብኝ ተስፋ አለኝ ፡፡ አቶ ያሬድ ጥበቡ ’’ በዚያ ትውልድ’’ ጥያቄና ትግል ውስጥ ጥርሳቸውን ነቅለው ያረጁ ሰው ስለሆኑ ፣ እኝህን ሰው ቀና ብሎ መተቸቱም ትንሽ ውስጤን ተጋዳሮታዊ ስሜት ጭምር አንገላቶት ነበር ፡፡ ባጠቃላይ ግን ወቅታዊ በሆነው ዜና ላይ የአቶ ያሬድ የሰሞኑ አቋማቸው ብቻ ሳይሆን ከዚህ በፊትም ካልተሳሳትኩ አንድ አመት ግድም ይሆነዋል ’’ ልቤን መልስልኝ ’’ በሚል ርዕስ ስለቀድሞው ጓዶቻቸው ወይም ጉዶቻቸው ለአቶ በረከት ሰምዖን እና አቶ አዲሱ ለገሰ የናፍቆት ስቃይ ፣ በኤሮግራም የጻፉላቸውን ግልባጭ ለዲያስፖራው ኢትዮጵያዊ ማስነበባቸውም ትዝ ይለኛል ፡፡
አቶ ያሬድ በዚያ ልቤን መልስልኝ ጽሁፋቸው ላይ ፣ አሁንም ድረስ የበረከት እና አዲሱ ለገሰ ሳቅ ፊታቸው ላይ ግጥም እያለ ! ሳቃችው ናፈቀኝ የሚያሰኝ ዛር እያሰቃያቸው እንደሆነ አስነብበውናል ፡፡በዚያን ወቅት ለአቶ ያሬድ ጥበቡ ጽሁፍ የመልስ ምት የሰጠ ሰው እንዳለ ባላስታውስም ፣ አቶ ያሬድ የዘፈን ዳድ ዳሩን ጨዋታ ዛሬ ብቻ ሳይሆን ቀደም ብለውም ሞክረውት ነበር ፡፡ ይኽ ደግሞ መብታቸው ነው ፡፡
ነጋድራስ ተሰማ እንደተቀኙት ቁልፉን በእጃቸው ይዘው አቶ ያሬድን አላስገባ ያሏቸው ሰው ደግሞ ! በሞትም ሆነ ህይወት በፈጣሪ እጅ ስለወደቁ ፣ ቁልፉን የሚረከበው የቀድሞው ጓዴ ነው የሚል ፖለቲካዊ- እሳቤ አቶ ያሬድ ተሰምቷቸው ነው የአቶ በረከትን ’’ እዉነተኝነት ’’ ምስክር እየሰጡ የሚገኙት የሚለውንም የብዙ ሰዎች ሃሳብ እንድጋራ ልቤ እየተፈታተነኝ ነው ፡፡ አቶ ያሬድ ግቡን ያልመታውን የተማሪዎች ጥያቄ ንቅናቄን ፣ ለማስመለስ እስከአሁን በስደት ለሃያ አምስት አመታት እየተሰቃዩ እንደሆነ ቢታወቅም ፣ እድሜ ሲገዝፍ የሚያመጣውን የአመለካከት ለውጥ ባምንበትም እንዲህ ሸብረክ ብለው ግን እጅ በጠዋቱ ይሰጣሉ የሚል እምነት አድሮብኝም አያውቅም ነበር ፡፡
አሁን ግን ከሳቃችሁ ናፈቀኝ ! ጀርባ ባለተረኛውን አድንቆ በመጪው ካቢኔ የመጠርነፍ ስሜት የተሰማሆት ስለመሰለኝ ነው ይህን ጽሁፌን ባክብሮት ያቀርብኩልዎ !! ፡፡ የፖለቲካ- እሳቤንና መጪውን አትርፊና ኪሳራ ጨዋታ ደግሞ በትግል ተሞክሮዎት፣ የበለጠ ስለሚያውቁት ፣ በዚህ ኪሳራ ውስጥም ይዘፈቃሉ ብዬ አላምንም ፡፡ የነብርን ጭራ አይያዙ ! ከያዙም አይልቀቁ ነውና ስደት ቢያንገሸግሽዎትም እስከዛሬ ድረስ የታገሉለትን ዓላማ እርግፍ አድርገው ጥለው ፣ በነበረከት ’ሳቅ ናፍቆት እጅ ይሰጣሉ ብዬም አላምንም ፡፡ ከሰጡ ግን ፣ ምናልባት ይህ የፈረንጆች ቀልድ በአጭሩ ከትንሽ ፈገግታ ጋር አንድ ነገር ፈንጠቅ ያደርግልዎታል ብዬ አምናለሁ ፡፡
Son: Dad, how much does it cost to get married. Father: I never calculated, I am still paying for it.
ከምርጫ ዘጠና ሰባት በኋላ በትክክል ቀኑንና ዓመተ ምህረቱን በማላስታውስበት ወቅት ፣ ’’ይህችም ከተማ ሆና ! ቂጥኝ አፈራች እንዲሉ ! ’’ ማንንም በማትደብቀው ፣ በጠባቧና በትንሿ የኖርዌይ ኦስሎ ከተማ ውስጥ ሁለት ጎምቱ ፖለቲከኞችን ዓይኔ ያያል፡፡ በሃገራችን ጉዳይ ላይ የድንበር ቂም ያላት የምትመስለው ኖርዌይ ዘወትር በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ የማትሰበሰበው ነገር የለምና ፣ ከስብሰባ መልስ ለረፍት ሽርሽር የወጡትን ፣ አቶ ያሬድ ጥበቡንና አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን እዚያችው ትንሿ ኦስሎ ከተማ ውስጥ አያቸዋለሁ ፡፡ ነገሩ ከነከነኝና ፣ ከኋላ ኋላቸው እንደ ፊርማ ቶሪ የሚገቡበትን ቦታ ለማወቅ ተከታተልኳቸው ፡፡ ሂደው ሄደው ካረፉበት ሆቴል ሲገቡ ተመልከትኳቸው፡፡
በሃገራችን ጉዳይ ላይ ከፍተኛ ተሳትፎ የነበራቸውን ፣ አሁን በስደት ኦስሎ ነዋሪ የሆኑትን ሁለት አንጋፋ ሰዎች ፣ ስላየሁት ነገርና ኖርዌይ ውስጥ ምን እየተሠራ እንደሆነ የሚያውቁት ነገር እንዳለ ጠየቅኋቸው ፡፡ እነኝህ ሁለት ሰዎች ምንም የሰሙት ነገር እንደሌለና የነገርኳቸውም ነገር ግርታ እንደፈጠረባቸው ይመልሱልኛል ፡፡ ሁኔታውን በአንክሮስንከታተል፣ የተረዳነው ነገር ቢኖር ፣ ኦስሎ በሚኖሩት አቶ ለንጮ ለታ አስተባባሪነት ፣ በኖርዌይ መንግሥት የበጀት እገዛ አንድ የተቃዋሚዎች ስብስብ ስብሰባ እንደተካሄደ ወሬው ይሰማል ፡፡ በዚህ ስብሥብ ውስጥ ፣ ከአገር ቤት ጭምር እነ አቶ ገብሩ አስራትን ፣ እነ የማነ ጃማይካን የመሳሰሉ ሰዎች ሁሉ የተካተቱበት እንደነበር ይረጋገጣል ፡፡ የዚያ ስብሰባ ዓላማና ምንነት እስከአሁን ድረስ ለኢትዮጵያ ህዝብ በግልጽ የተነገረ አይመስለኝም ፡፡ ኧንዲያውም ስብሰባው ሲቋጠር ቀጣይ የሆነ ስብሰባ እንደሚዘጋጅም ጭምር ነበር ፡፡ አቶ ያሬድ በዚህ ስብሰባ ላይ ማንን ወክለው እንደተገኙ ባይታወቅም፣ በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ግን ጊዜ በሚያመጣው የፖለቲካ እንቅስቃሴ ውስጥ ቢያንስ ከጀርባ እንዳሉ የሚያሳይ ነው የኦስሎው ተሳትፎዎ ! ፡፡ ይህ ደግሞ የሚያሳየው ! የአቶ መለስን ህመም ወይም ሞት ተከትሎ ፣ ዜናው ለርሶ የተደበቀ አይመስለኝም ፡፡
በአውራምባ ታይምስ ላይ ፣ የቀድሞው ሳቁ የናፈቀዎትን ጓደኛዎን ሃቀኝነት ለመመስከር ሲሉ ፣ የበረከትን እውነተኝነት ልክ የጦር ሠራዊት ሲግናል ወታደሮች ’’ሞርስ’’ ብለው የሚተረጉሙትን የቃላት ንዝረት ስኬል በመለካት የበረከት ምላስ አትልም ላስ !!- የሚል እንደምታ ያለው ቃል ከመሰንዘርዎ ውጭ ፣ የዲያስፖራው ሚድያና እንዲሁም አንዳንድ የፖለቲካ አላዋቂነት ችግር ያለባቸው በማለት የኮነኑበት የቃላት ንጥቀት ፣ ልክ አቶ በረከት እንዳለው ’’ክፋት ’’ ቃሏን እርሶም ደግመዋታል እጅግ አሳዛኝ አባባል ትመስለኛለች ፡፡ ምናልባት አልታወቀዎት ይሆናል እንጂ የኮሚኒኬሽን ሚንስቴሩን የሥራ መደብ ርስዎ የሚሠሩት አስመስሎዎበታል፡፡
በዚህ ወቅት ሊከሰት የሚችለውንም አደጋ አስመልክቶ ፣ ህዝቡ ወይ ተባበሩ አለዚያም ተሰባበሩ ያላቸውን ተቃዋሚዎች ፣ በአሁኑ ወቅት ያደረጉትን መሰባሰብ ፣ እጅግ በማቅለልና በመኮነን ፣ ተቃዋሚዎች በዚህ ወቅት በፍጥነት መሰባሰባቸውና መደረጀታቸው የሚገርም ነው ያሉት ሳያንስ ፣ ምዕራባውያን ከብዙ መቶ ዓመታት በፊት ያከማቸቱን ልምድ በውጭ በመኖራችን በመላመዳችን ለምን እንደዚህ አልሆነም ብሎ ዲያስፖራው እነበረከትን መውቀሱም ትክክል አይደለም የሚል እንደምታ መጠቀምዎ ጭምር ትንሽ የነበረዎትን ያክብሮት ቦታ የሚሸረሽርብዎት ይመስለኛል ፡፡
በረከት ! ዉሸታም ለመሆኑ እስከዛሬ የተናገራቸውን በዝርዝር ቁጥር በቁጥር ማቅረብ ይቻላል ፡፡ በቅርቡም የጻፈው መጽሃፉ ማስረጃ ነው ፡፡በምርጫ 97 ወቅትም በቡግና ምርጫ ጣቢያ የገለበጠውም የህዝብ ድምጽ አንድ ትልቅ ሃሳዊ ሰው መሆኑን ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ሃቅ ነው ፡፡ ከዚያ ሁሉ በላይ ደግሞ በለጋነቱ ወቅት በኢህአፓ ውስጥ የታገለበትን ህብረ ብሄር ትግል አፍርሶ ፣ በዘር ከረጢት ውስጥ ራሱን በመቋጠር የዘረኝነት መርህን የተከተለ ሰው ፣ ዛሬ ! በረከትን ሳውቀው ካፉ ጠብ የሚል ዉሸት የለውም ብሎ መመስከር ተገቢ አይመስለኝም ፡፡
በምርጫ 97 ወቅት ሁለት ሕጻናት ልጆቻቸው የተገደሉባቸው እናት ፣ ዛሬ የመለሰንና የበረከትን መንግሥት ዝና ሲያጎሉላቸው ቢሰሙ ምን ይሉዎት ነበር ? በሱማሊያ ጦርነት እሰው አገር ላለቁት ኢትዮጵያውያን ወታደሮች የት እንደደረሱ የተጠየቀው የመለስና የበረከት መንግሥት ፣ ምን አገባችሁ ? የመመለስ ኃላፊነት የለብንም ያለን መንግሥት ፣ ልጇ የሞተባት ከል የለበሰች እናት ይዟቸው ይሂድ ብትል ፣ የለም ኢትዮጵያዊ ባህል አይደለም ብለው የሞራል ትምህርት ሲሰጡ ትንሽ ዘግነን አላለዎትም ?
የስንቱ ቤት በነኝህ ሁለት ሰይጣናት ፈረሰ ? ምንስ ስልጣንና ዝና ቢናፍቅ ! ምንስ ስደት ቢያንገሸግሽ ፣ ለበረከት ሲባል የዲያስፖራው ሚዲያ ፣ ተቃዋሚ ሁላ መንኳሰስ አለበት ? በውጭ ያለው የፖለቲካ አካሄድ እንዲታረቅና ጉድለቱንም ሆነ ችግሩን ማሳየት በተለይ እንደርስዎ በትግል የጎለመሰና በቂ እውቀት ያለው ሰው ትችታዊ ወቀሳ ተገቢ ቢሆንም ፣ በአውራምባ ታይምስ ላይ በሰጡት ቃለ- መጠይቅ ግን አቶ ሽመልስ ስለ -ጌታው በረከት ሰምዖን ቢጠየቅ ሊሰጠው ወደሚችለው ምስክርነትን ዓይነት ቃለ መጠይቅ ነው የመሰለብዎ ፡፡

ኢትዮጵያ ለዘላለም ከነሙሉ ክብሯ ትኑር !! 
እንግዳ ታደሰ 

3 comments:

  1. ይህ ሰውዬ ፊቱም ንግግሩም የሸርሙጣ ነው!!!

    ReplyDelete
    Replies
    1. abete yafe qelate!!ayebalem zanederom atemarum senasereate

      Delete
  2. Wonderful article. This is good. The man appears as a moral person, symphatising for Meles, but he never showed symphaty for the victims Meles and his party has victimised since 1991. Such person should never have stake on Ethiopian politics. Such persons are like Esau who sold their birth right , noble principle for a peice of food, money and power.

    ReplyDelete