Friday, August 17, 2012

መገፋት የወለደው የኢትዮጵያ ወጣቶች የመነሳሳት አዝማሚያ

በነብዩ ኃይሉ    


የተባበሩት መንግስታት ጠቅላላ ጉባኤ እ.ኤ.አ በ1999 ዓ.ም ባስተላለፈው ውሳኔ መሠረት ለ12 አመታት በየአመቱ ኦገስት 12 የሚከበረው የአለም የወጣቶች ቀን ከትላንት በስቲያ እሁድ ነሐሴ 6 ቀን 2004 ዓ.ም በኢትዮጵያ በተቃርኖ ታጅቦ ተከብሯል፡ ፡ በዕለቱ የገዢውን ፓርቲ መዝሙር የሚያዜሙት የወጣቶች ፎረምና የወጣቶች ሊግ የተውጣጡ አባላት በአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት የአለም የወጣቶች ቀንን ሲያከብሩ፣ ከገዢው ፓርቲ በተለየ ኢትዮጵያዊነት ላይ አትኩሮ ለመስራት የተቋቋመው የባለ ራዕይ ወጣቶች ማህበር አባላት ለህይወታቸው በሚያስጋ መልኩ በታጣቂ ፖሊሶች ስብሰባ እንዳያደርጉ ተበትነዋል፡፡ ይህ አይነቱ ክስተት አጋጣሚ የወለደው ሳይሆን የአቶ መለስ መንግስት የማይቀየር ባህሪ ማሳያ ነው፡፡
መንግስት በአምሳሉ የፈጠራቸውን ጥቂት ቡድኖች አቅርቦ፣ የተለየ አስተሳሰብ ያላቸውን ገሸሽ ከማድረግ አልፎ ህልውናቸውን የሚያጠፋ እርምጃ ለመውሰድ ሀይሉን አይቆጥብም፡ ፡ ይህ ጽሁፍ የወጣቱንና የኢህአዴግን የ21 አመት ግንኙነት፣ የኢትዮጵያን ወጣቶች መገፋትና የመነሳሳት አዝማሚያ ማሳያዎችን ይዳስሳል፡፡
ወጣቶችና የኢህአዴግ ግንኙነት
በስልጣን ላይ ያሉት አብዛኞቹ የህወሓትም ሆነ የኢህአዴግ ባለሟሎች፣ በወጣትነታቸው በፀረ-ጭቆና ትግል ውስጥ ለመግባት የቆረጡ ናቸው፡፡ ደርግን አስወግደው ወደ ምኒልክ ቤተመንግስት ሲዘልቁም ታጋዮቹ አቶ መለስን ጨምሮ ብዙም ከወጣትነት ባልራቀ እድሜ ላይ ነበሩ፡፡ ይህ የታሪክ አጋጣሚ ለእነ አቶ መለስ የኢትዮጵያን ወጣት ፍላጐት ለመረዳት የሚያስችላቸው ቢሆንም፤ ገና ከጅምሩ ከወጣቶች ጋር በሚኖራቸው ግንኙነት ላይ እሾህ የመነስነስን መንገድ ተከትለዋል፡፡ ለዚህ ጽሁፍ በሚመች መልኩ የኢትዮጵያን ወጣቶችና የኢህአዴግን የ21 ዓመታት ግንኙነት በሶስት መደብ ከፍሎ መመልከት ይቻላል፡፡
ቅድመ ምርጫ 97፡- ይህ ወቅት ኢህአዴግ ወጣቶችን ሙሉ በሙሉ የገፋበት ወቅት ይመስላል፡፡ መንግስት ስራ አጥተው የሚንከራተቱ ወጣቶችን “አደገኛ ቦዘኔ” የሚል ታፔላ በመስጠት የተለያዩ እስሮችና የማንገላታት እርምጃዎችን የወሰደበት እንደነበር የፈፀመበት እንደሆነ በብዙዎች ይታመናል፡፡ ይህ አይነቱ የመንግስት ግብታዊ እርምጃ ወጣቱን ወደ ተቃውሞ ጐራ እንዲያዘም አድርጐታል፡፡ ለዚህም ይመስላል በምርጫ 97 ዋዜማ ኢህአዴግ ያቀረባቸውን የተለያዩ ማባበያዎች “አደገኛ ቦዘኔ ራሱ ወያኔ” የሚል ዜማ በማቀንቀን ለተቃዋሚዎች ድጋፍ የሰጠው፡፡ ኢህአዴግ በምርጫ 97 የደረሰበትን አስደንጋጭ ሽንፈት ተከትሎ በተፈጠረው ውዝግብ ቀዳሚ ተጠቂ የሆነውም ወጣቱ የህብረተሰብ ክፍል ነው፡፡
በአቶ መለስ መንግስት ከሃያ ሺ በላይ ወጣቶች በእስር ቤቶችና በወታደራዊ ካምፖች ከታሰሩ እና ከ200 ያላነሱ ባብዛኛው ወጣት የሆኑ ንፁሀን ዜጐች በአደባባይ ከተገደሉ በኋላ፣ ኢህአዴግ ወጣቶችን ለማቅረብ የሚያስችሉ ብልጣብልጥ ዘዴዎችን ቀየሰ፡፡ ወጣቶችን በተለያዩ ጥቅማ ጥቅሞች ዙሪያ በማሰባሰብ በወጣት ፎረም፣ በወጣት ሊግ አደረጃጀት ለመቆጣጠር የሚያስችል መንገድ ቀየሰ፡ ፡ በእነዚህ አደረጃጀቶች የታቀፉ ወጣቶችም “እንደ በኩር ልጅ” የተለያዩ ጥቅማጥቅሞችን ከመንግስት የሚያገኙበት፣ ተፃራሪ አልያም የተለየ አመለካከት የሚከተሉ ወጣቶች ምንም አይነት እድል የተነፈጉበት አካሄድ ታይቷል፡፡
ድህረ ምርጫ 97፡- ምርጫ 97ን ተከትሎ
ወቅታዊው ሁኔታ፡- ኢህአዴግ በድህረ 97 የተከተለው ጥቅም ተኮር የአባላት ጅምላ ጠመቃ እና ለአገዛዝ በሚመቸው መልኩ የማደራጀት ተግባር ወጣቱን ወደ መንግስት እቅፍ ያሰባሰበው ቢመስልም፣ መንግስት ያለውን ሰምተው የተጠጉትን ወጣቶች ጥያቄ በአነስተኛ ደረጃ እንኳን ማሟላት በማይችልበት ደረጃ ደርሷል፡፡ ከከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተመርቀው የኢህአዴግ አባል ሳይሆኑ በሰለጠኑበት ሙያ መስራት አለመቻል ተመራቂዎችን ለኢኮኖሚያዊ ጥቅም ሲሉ ወደ ፓርቲው ሊሳቡ ቢችሉም፣ ለተመራቂዎቹ ከኮብልስቶን ጠረባ የተሻለ ስራ ሊያቀርብላቸው አልቻለም፡፡
ከላይ የተመለከቱት የኢህአዴግንና የወጣቱን ግንኙነት የሚያመላክቱ ነጥቦች በግልጽ እሚያስረዱት በስልጣን ላይ ያለው ስርአት የወጣቶችን ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊና ማህበራዊ ፍላጐት ለ21 አመታት ለመመለስ አለመቻሉ ነው፡፡ ከዚያም ባለፈ ወጣቶች ጥያቄያቸውን/ፍላጐታቸውን ለማንሸራሸር የሚችሉበት አግባብ የተዳፈነ መሆኑ፣ ኢትዮጵያን የተገፉ ወጣቶች የበረከቱባት ሀገር አድርጓታል፡፡
ወጣቶችን የመግፋት ውጤት
“ወጣትነት ለውጥ እንደ ውሃ የሚጠማበት፤ ለለውጥ መስዋዕትነት መክፈል እንደ ታላቅ ተግባር የሚወደስበት ነው” የሚለው ወጣት ኢድሪስ በማህበራዊ ሚድያዎች በተለይም በፌስ ቡክ ላይ መንግስት የሚፈፅማቸውን የመብት ጥሰቶች በማጋለጥ በሚታወቁ የቡድን ገጾች ላይ በሚጽፏቸው አስተያየቶች ይታወቃል፡፡ በወጣቱ እምነት የሀገር ሁለንተናዊ ህልውና የሚወሰነው ወጣቶች ባላቸው ሚና ላይ ነው፡፡ በተለይም ከኢትዮጵያ የህዝብ ቁጥር ውስጥ የወጣቶች ቁጥር ከፍተኛ መሆኑ ከላይ የቀረበውን አስተያየት ሚዛን የሚደፋ ያርገዋል፡፡
ፍላጐታቸውን ለማሟላትም የኢህአዴግ እቅፍ ውስጥ መሸጐጥ አማራጭ የሌለው ግዴታ እንደሆነባቸው ይነገራል፡፡ ይህ ወጣቶችን የመግፋት አካሄድ ወጣቶች መብታቸውን ለማስከበር እንዲነሱ የመገፋፋት አቅም አለው፡፡
ወጣቶች በየትኛውም የአለም ክፍል በምርጫ ወይም፣ በተለያዩ ብዙሃን ማህበራት የመሳተፍ የበረታ ተነሳሽነት እንደሌላቸው በርካታ ጥናቶች ያስረዳሉ፡፡ ጉተንበር ዩኒቨርሲቲና ስቶኮልም ዩኒቨርስቲ በጋራ በሰሩትና ‹‹young people & political consumerism›› የሚል ርዕስ በሰጡት ጥናት እንዳሳዩት፣ የወጣቶች ፖለቲካዊ ተሳትፎ ከ40 አመት በላይ በሆኑ ጐልማሶች ተወስዷል፡፡ ይህ ሁኔታ በኢትዮጵያ ፖለቲካም በግልጽ ይታያል፡፡ ወጣቶች በኢትዮጵያ ፖለቲካ ቦታ ያላቸው አይመስልም፡፡ የባለራዕይ ወጣቶች ማህበር አመቻች ኮሚቴ ሰብሳቢ የሆነው ወጣት ሀብታሙ አያሌው “የኢትዮጵያ ወጣቶች ከሀገራቸው ፖለቲካ እንዲገለሉ ተደርገዋል” ብሎ ያምናል፡፡ ኢኮኖሚያዊ
በሰሜን አፍሪካ አብዮት በአብዛኛው የወጣቶች መገፋት የወለደውና በወጣቶች የተመራ ነበር፡፡ ስራ አጥነት፣ የከፋ ሙስና እንዲሁም የሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብት ጥሰቶች ያቀጣጠሉት የአረቡ አለም መነቃቃት ለኢትዮጵያ ወጣቶች የሚያስተላልፈው የሞራል ስንቅ አለው፡፡ በኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ በግልጽ እንደሚታየው ሁሉም ዜጋ ላይ የሚፈፀሙ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ በደሎች ቢኖሩም፣ በወጣቶች ላይ የተጫኑት የበደል መርጐች ግን የሰሜን አፍሪካ ወጣቶችን ወደ አደባባይ ተቃውሞ ከጠሩት እጅግ የከበዱ ናቸው፡፡
የኢትዮጵያ ወጣቶች እነዚህን ችግሮቻቸውን ለመፍታት የሚሄዱባቸው የትኞቹም ፖለቲካዊ አግባቦች በአሸባሪነት ላለመፈረጃቸው ዋስትና የላቸውም፡፡ ለዚህ ማሳያ የሚሆኑት በሀገራቸው ፖለቲካ ለመሳተፍ የተቃዋሚዎችን ጐራ የተቀላቀሉ ወጣት ፖለቲከኞች እና በተለያዩ ጋዜጦች ላይ ሀሳባቸውን ለመግለጽ ጥረት ያደርጉ የነበሩ ወጣት ጋዜጠኞች ከአቶ መለስ መንግስት የተለየ አቋም በመያዛቸው ብቻ በአሸባሪነት ተከሰው ወደ እስር መጎተታቸው ነው፡፡ መንግስት የሚወስዳቸው እነዚህ ገፊ እርምጃዎች ወጣቶች እጃቸውን አጣጥፈው እንዲቀመጡ አላደረገም፡፡ የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ የሆነው ወጣት ደንኤል ተፈራ እንደሚያስረዳው መንግስት በቅርቡ በወጣት ጋዜጠኞችና በተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች ላይ የወሰደውን የእስር እርምጃ ተከትሎ ከመቼውም ጊዜ በበለጠ አንድነት ፓርቲን የሚቀላቀሉ ወጣቶች ቁጥር ጨምሯል፡፡
መንግስት በሀይማኖት ላይ የሚያደርገውን ጣልቃገብነት በመቃወም ከሰባት ወራት በላይ የዘለቀውን የሙስሊሞች ተቃውሞ በመምራት እንዲሁም በግንባር ቀደም ተሳታፊነት የሚካፈሉት ወጣቶች መሆናቸው ለመንግስት እንቅልፍ የሚነሳ ሆኗል፡፡
ኢድሪስ የወጣቶች በመንግስት መገፋት አንገብግቧቸው በማህበራዊ ሚዲያዎች ወጣቱን ከሚቀሰቅሱ ንቁ ወጣቶች መሀል ይመደባል፡፡ የነኢድሪስ ቡድን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከኢንተርኔት ግንኙነት ባለፈ የገፅ ለገፅ ውይይቶችን ጀምሯል፡፡ የወጣቶቹ መሰባሰብና መወያየት ወደ ተግባራዊ ተቃውሞ የማደግ ውጤት ሊኖረው ቢችልም፣ መንግስት የአደባባይ ውይይቶችን በክፉ ማየቱ የወጣቶቹ በስጋት እንዲንቀሳቀሱ አድርጓቸዋል፡፡ እነዚህ ድምር የመገፋት ውጤቶች የወለዷቸው የመነሳሳት አዝማሚያዎች በሀገሪቱ ፓለቲካዊ ለውጥ ውስጥ ምን አይነት ሚና ይኖራቸዋል?
የኢትዮጵያ ወጣቶች የመነሳሳት አዝማሚያ ምልክቶች
ያስገነዝብ ነበር፡፡ የኢትዮጵያ ወጣቶችም ይህን ተሞክሮ ያብሰለሰሉት ይመስላል፡ ፡ ኢሳም ፋሬስ ኢንስቲትዩት ፎር ፐብሊክ ፖሊስ ኤንድ ኢንተርናሽናል አፌርስ የፖሊሲ ጉዳዮች ላይ አተኩሮ የሚሰራ ተቋም ነው፡ ፡ ተቋሙ የአረቡ አለም መነሳሳት ከመከሰቱ አስቀድሞ በተጨባጭ አብዮት ሊያስከትሉ የሚችሉ፣ የአረቡ አለም ወጣቶች ችግሮችን ነቅሶ ጠቁሞ ነበር፡፡ ይህ የፖሊሲ ተንታኝ ተቋም ጃንዋሪ 13-14 2009 ባዘጋጀው ሴሚናር ላይ “studying youth in the Arab world” በሚል ርዕስ ያቀረበው ጥናት ስራ አጥነት እና የዴሞክራሲ መነፈግ የአረብ ወጣቶችን ወደ አደባባይ ሊስብ እንደሚችል አስጠንቅቆ ነበር፡፡
የሰሜን አፍሪካ ወጣቶች የማይነቃነቁ የሚመስሉ ጠብደል አምባገነን መሪዎችን አሽቀንጥረው መጣላቸው ለአለም ህዝብ፣ በተለይም በፍፁማዊ አምባገነን ስርዓት ስር ሳሉ ህዝቦች “የማይወድቅ ስርአት” እንደሌለ
አረብ ሀገራት በኢኮኖሚ እድገት ረገድ በተከታታይ አመታት የተሻለ ውጤት ሲያስመዘግቡ የቆዩ ቢሆኑም እድገቱ የወጣቱን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ አለመሆኑ ወጣቶቹን ወደ አደባባይ እንዲወጡ አድርጓቸዋል፡፡ የአቶ መለስ መንግስት በተከታታይ አስመዝግቤዋለሁ የሚለው አወዛጋቢ “ባለ ሁለት አሀዝ” የኢኮኖሚ እድገት የወጣቱን ተጠቃሚነት እንዳረጋገጠ በተለያዩ አጋጣሚዎች ያትታል፡፡ ሆኖም ስርዓቱ አንድና ሁለት ዲግሪ የያዙ ሆኖም በስራ ማጣት ለጐዳና ተዳዳሪነት የተጋለጡ ዜጐችን ማፍራቱ፣ እንዲሁም ዲግሪ ጭኖ ኮብልስቶን ለመጥረብ እንኳን የኢህአዴግ አባል መሆን ቅድሚያ የሚሰጠው መስፈርት መሆኑ፣ በኢትዮጵያ ድንገተኛ መነሳሳት እንዲቀሰቀስ ከሚያደርጉ አዝማሚያዎች መሀከል በጉልህነት ሊጠቀስ ይችላል፡፡
“protests, movements & political change in the Arab world” በሚል ርዕስ ይፋ የተደረገው የካርኒጌይ ኢንዳውመንት ፎር ኢንተርናሽናል ፒስ የተሰኘው የፖሊሲ አጥኚ ተቋም ጥናትም የአረቡን አለም መነሳሳት በሚከተለው መልኩ አስቀምጦታል፤ “በቱኒዝያ የተጀመረው እና መላ አረብ ሀገራትን የናጠው መነሳሳት ድንገት የፈነዳ ክስተት አይደለም፡፡ ይልቁንም በአካባቢው ሀገራት ባለፉት አስር አመታት የተጠራቀመ የህዝብ ብሶት ውጤት ነው፡፡” እንደ ጥናቱ ግምገማ የአካባቢው ሀገራት በተለይም ግብጽ፣ ሞሮኮ፣ አልጄሪያና ዮርዳኖስ ላለፉት አስር አመታት በተለይ የወጣቶች ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጥያቄዎች ሲብላሉባቸው የኖሩ ናቸው፡፡ የኢትዮጵያ ወጣቶች ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊና ሃይማኖታዊ ጥያቄዎች ለ21 አመታት በመንግስት ችላ ተብለው መታለፋቸው በለሆሳስ እንዲብሰለሰል ማድረጉ በሀገሪቱ ድንገተኛ መነሳሳት ሊፈጥር እንደሚችል ተጨባጭ ፍንጭ ይሰጣል፡፡ ለዚህ አባባል በቅርቡ በሆሳእና ተመርቀው ስራ ያጡ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች መንግስት ስራ እንዲሰጣቸው በተደራጀ ሁኔታ የጠየቁበት መንገድ ለዚህ ሁነኛ ማሳያ ሊሆን ይችላል፡፡
ከሰባት ወራት በላይ በወሰደውና በተደራጀ መልኩ መንግስት ከሃይማኖታቸው ላይ እጁን እንዲያነሳ እየጠየቁ ያሉት በአብዛኛው ወጣት የሙስሊሙ ማህበራሰብ አባላት፣ የመንግስት የኃይል እርምጃ እና እስር በጽናት ተቋቁመው መቀጠላቸው ሌላው የኢትዮጵያ ወጣቶችን የመነሳሳት አዝማሚያ ያመላክታል፡፡
ለወጣቶች ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጥያቄዎች ተገቢውን ትኩረት የነፈገው የኢህአዴግ መንግስት ድርጊት ስርዓቱን የኋላ ኋላ ዋጋ ሊያስከፍለው እንደሚችል አያጠያይቅም፡፡ ምንጭ :       http://www.fnotenetsanet.com

 

No comments:

Post a Comment