Sunday, August 26, 2012

ዜና እና ደብዳቤ፤ በሀዋሳ ከተማ የአቶ መለስን ፎቶግራፍ ሲያሳይ የነበረ “ስክሪን” በመብረቅ ተመታ!


ዜና እና ደብዳቤ፤ በሀዋሳ ከተማ የአቶ መለስን ፎቶግራፍ ሲያሳይ የነበረ “ስክሪን” በመብረቅ ተመታ!

አንድ ወዳጄ አሁን ከሀዋሳ ባደረሰኝ መልዕክት በሐዋሳ መስቀል አደባባይ የመለስን ፎቶግራፍ እና ቪዲዮ ሲያሳይ የነበረ ስክሪን በመብረቅ ተመቷል። እንደው መረጃውን ላድርሳችሁ ብዬ እንጂ በዚህ ጉዳይ ላይ ምንም የምሰጠው አስተያየት የለኝም።
ሀዋሳ ካልኩ አይቀር እና ከመጣሁ አይቀር ግን ትላንት ከዚሁ ከሀዋሳ የደረሰኝ ኢሜል “እንደ ወረደ” እንደሚከተለው ይቀርባል።
የኢትዮጵያ ጠ/ሚ መለስ መሞት አስመልክቶ ለለቅሶ ተገደን የምንወጣበት ምክንያት አልገባኝም፡፡
በተለይ እዚህ እኔ ባለሁበት ሀዋሳ የሚሆነው ነገር ግራ የሚያጋባ ነው፡ በየቀበሌው ድንኳን ተጣለ፤
ለቅሶ ድረሱ ተባለ፤ የቻለ መሄድ ሲገባው፤ እየተሰራ ያለው ነገር ግን የሚያስፈራ ነው፡፡ በደቡብ ድምጽ ራድዮ የተነገረው ማስታወቂያ  “መስቀል አደባባይ እየሄዳችሁ ሀዘናችሁ ግለጹ” ነበር ሆኖም ግን በዚህ ብቻ አላበቃም፡፡ ይህንንም በተመለከተ በየ መስሪያ ቤቱ ማስታወቂያ ተለጠፈ፤ ይህም አልበቃ ብሎ “ቅዳሜ በ19/12/04 ዓ.ም. በ4፡00 ሰዓት ጥቁር ልብስ ለብሳችሁ፡ የመለስ ፎቶ ይዛችሁ መፈክር አዘጋጅታችሁ መስቀል አደባባይ ተገኙ” የሚል ወረቀት ተበተነ፡፡ ይህም አንሶ ነው መሰለኝ እነደገና ቤት ለቤት እየዞሩ እየቀሰቀሱ ውጡ ሀዘናችሁ ግለጡ ብለው እስገደዱን ነው፡፡ እኔ ያልገባኝ ምንድነው ትርፉ ከዚህ ቅስቀሳ? እኔም ተገድጄ ቢሮዬ የኢንተርኔት አገልግሎት እንዲቋረጥ አድርገው ሁሉም ሰራተኛ እንዲወጣ ስላደረጉ ወጣሁ ነገ በስራዬን ሊገጥመኝ የሚችለው ነገር በመስጋት፡፡ እንደዚህ መሆኑን አግባብነው? እባካችሁ መለስም ቢሆኑ በሰብአዊ መብት ረገጣ የሚወቀሱበት የነበረው፡ ካድሬዎች እንደዚህ ህዝቡን አፍነው አስፈራርተው እንዲወጣ ካደረጉት በኋላ “ህዝቡ እንደዚህ ነው ይደግፈናል” እያሉ ሲያታልሉ የነበሩበት መንገድ ነው፡፡
አሁንም ቢሆን ህዝቡ እነሱ እነደሚሉት ለመሪው ካለው ፍቅር የተነሳ ብቻ አለመሆኑን መታወቅ አለበት፡፡ ተገዶም ጭምር ነው፡፡
እንደኢህ እራስን እታለሉ መኖር ጉዳቱ የከፋ ስለሚሆን አንድ ሊባል ይገባል፡፡
ማቴዎስ ከሀዋሳ

ምንጭ ;http://www.abetokichaw.com/2012/08/26/ ዜና-እና-ደብዳቤ፤-በሀዋሳ-ከተማ-የአቶ-መለ/

No comments:

Post a Comment