Thursday, September 6, 2012

የፍኖተ ነጻነት ምክትል አዘጋጅ ተደጋጋሚ የግድያ ማስፈራሪያ እንደደረሳቸው አስታወቁ


የፍኖተ ነጻነት ምክትል ዋና አዘጋጅ የሆኑት አቶ ብዙአየሁ ወንድሙ ለኢሳት እንደገለጡት በተለይ ከአቶ መለስ ዜናዊ ሞት በሁዋላ በተደጋጋሚ ” በቅርብ ቀን ትገደላለህ ” አቶ መለስ ከመቀበሩ በፊት አንተ ትቀበራልህ የሚል የስልክ መልእክት ሲደርሳቸው መቆየቱን አውስተው፣ በዛሬው እለትም ተመሳሳይ መልእክቶች ሲደርሳቸው መዋሉን ተናግረዋል::
“ጉዳዩን ለፖሊስ አመልክተዋል ወይ?” በሚል ከኢሳት ለቀረበላቸው ጥያቄ፣ የህግ ባለሙያዎች ተመሳሳይ ምክር ቢሰጡዋቸውም፣ በህግ ተቋሟት ላይ እምነት የሌላቸው በመሆኑ እስካሁን ሳያመለከቱ መቆየታቸውን አቶ ብዙሀአየሁ ተናግረዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ አንድነት ፓርቲ ፍኖተ ነጻነት ጋዜጣ ታግዶ እጁን አጣጥፎ እንደማይቀመጥ የፓርቲው ከፍተኛ አመራር ተናግረዋል።

የአንድነት ፓርቲ የብሄራዊ ምክር ቤት ሰብሳቢ የሆኑት አቶ ዘካርያስ የማነአብ እንደገለጡት ፓርቲው በልሳኑ ላይ የተጣለበትን እገዳ ለመቃወም  ህዝቡ ወደ አደባባይ እንዲወጣ ጥሪ እስከማድረግ የሚደርስ እርምጃ ይወስዳሉ::

No comments:

Post a Comment