Wednesday, August 7, 2013

ጴጥሮሳዊነት

/መሰፍን/ማርያም

ቀደምሲል « እግዚአብሔርና እኛ» በሚለው ርዕስ ስር የተነገረውን አንዳንድ ሰዎች ሌላ ትርጉም በመስጠት ጸረሃይማኖት ሊያስመስሉት ይሞክሩ ይሆናል። አይደለምእንዲያውም ሃይማኖትንና ሃይማኖተኛነትን የሚያጸናነው። የኢትዮጵያ ሕዝብ ምንም ዓይነት ሃይማኖት ቢኖረው ለእግዚአብሔር ያለው ፍቅርና በእግዚአብሔርም ላይ ያለው እምነት ብርቱ ነው።ይህንን ከመገንዘብ የተነሳና በዚያው ፍቅርና እምነት ላይ የተመሠረተ ስለሆነ በምንም መንገድ ጸረ ሃይማኖት መስሎ ሊታይ አይገባም።

ችግሩ ሌላ ነው። ችግሩ በኢትዮጵያ ውስጥ ለመንፈሳዊ ተግባርና ኃላፊነት የሚያበቃ ሁኔታ አለመኖርና ወደ ፍጹምነት የሚጠጋ የመንፈሳዊነት ድርቀት ነው። ... 1977 .. ጉለሌ በሚገኘው የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ውስጥ ለካቶሊክ ሚስዮናውያን ንግግር እንዳደርግ ተጠይቄ የኅብረተሰባችን የመንፈስ ውድቀት (ክስረት) በሚል ርዕስ በእንግሊዝኛ ተናግሬ ነበር። በዚያ ንግግር ውስጥ የሚከተለው በከፊል ይገኝበት ነበር።
በየቀኑ የጭካኔ ወሬ እንሰማለን። ወጣቱ ለወደፊት መዘጋጀቱን ትቶ፤ ክፉኛ ለሁለት ተከፍሎ እርስ በርሱ ለመጫረስ ተነሥቶአል። ለበለጠ ግድያና መጨራረስ ጩኸት እንሰማለን፤ የእናቶችና የሚስቶችን ጩኸት እንሰማለን፤ የሐዘን ልብሳቸውንም እናያለን። የሞትን አደጋ በየአቅጣጫው እናያለን። የፍቅርን አለመኖር እንሰማለን፤ እናያለን፤ የተስፋን አለመኖር እንሰማለን፤ እናያለን። ንዴትን እናያለን፤ እንሰማለን፤ ተስፋ ቢስነትን እንሰማለን፤ እናያለን፤ ሐዘንን እንሰማለን፤ እናያለን። ከዚህም በላይ ንዴቱም ተስፋ ቢስነቱም ሐዘኑም ይሰማናል። ሕይወት አጠራጣሪና በቀላሉ የሚጠፋ ሆኖአል። እንሰማለን፤ እናያለን፤ እናያለን፤ እንሰማለን። ምንም አናደርግም። ይህምንም ያለማድረግ ውሳኔና ይህ በኅብረተሰቡ ኑሮ ውስጥ ያገባኛል የሚል ስሜት መጥፋት ግልጽ የሆኑ የወላጆችን፤ የአስተማሪዎችንና የሃይማኖት መሪዎችን የመንፈስ ውድቀት የሚያመለክቱ ናቸው። ለግፍ፤ ለበደልና ለጥቃት እንድንገብር፤ ግፍን በደልንና ጥቃትን አየሰማንና እያየን ምንም እንዳናደርግ የሚያደርገን ምንድን ነው?
እኔ እንደ ሚመስለኝና እንደማምነውም የጉዳዩ ባለቤት ራሳችን መሆናችንን ተገንዝበን ኃላፊነቱንና የሚያስከትለውንም ውጤት ላለመቀበል የፈጠርነው የመከላከያ ዘዴ ጉዳያችንን ሁሉ ወደ እግዚአብሔር መወርወሩን ነው። የሚደንቀው ነገር የሃይማኖት መሪዎችን መለየቱ ለምን አስፈላጊ ሆነ? የሃይማኖት መሪዎች «ሥጋቸውን የበደሉ፤ ለነፍሳቸው ያደሩ» ናቸው ይባላል። የሃይማኖት መሪዎች ለጽድቅ ማለት ለእውነት እንዲሁም  ለፍትሕና ለእኩልነት የቆሙ ናቸው ተብሎ ይታመናል። ለሃብትና ለሥልጣን ግድ ስለሌላቸው ከዚህ ዓለም ጣጣው ጭናቸው ይባላል። እንግዲህ እንደዚህ ዓይነቶቹ ለእግዚአብሔር አድረናል የሚሉ ሰዎች ለግፍ ለበደልና ለጥቃት እንዲገብሩ የሚያደርጋቸው ከየት የመጣ ኃይል ነው? ከእግዚአብሔር ሊሆን አይችልም። ለዚህ ዓለም ሕይወት ካላቸው ጉጉት ብቻ የሚመነጭነው። የሚጎድላቸው ጴጥሮሳዊነትነው።
የአቡነጴጥሮስ መንፈስ እንደ ሐውልታቸው የተረሳ ይመስለኛል። አቡነጴጥሮስ እንደሌሎቹ ሁሉ ኢጣልያ ኢትዮጵያን የወረረችው «የእግዚአብሔር ፈቃድሆኖ ነው»በማለት የኢጣልያ ወታደር የኢትዮጵያን ሕዝብ አበሳውን ያሳየው በእግዚአብሔር ፈቃድ ነው በማለት ሊገብሩና የተደላደለ ኑሮ ለመኖር ይችሉ ነበር። አቡነጴጥሮስ የራሳቸውንና የአገራቸውን ጉዳይ ወደ እግዚአብሔር ሳይወረውሩ ኃላፊነታቸውን ሳይሸሹ «እምቢኝ አሻፈረኝአሉ። በእምቢተኛነታቸውም የኢጣልያንክርስቲያንነትና ሥልጡንነት ፈተና ውስጥ ከተቱት። በእምቢተኛነታቸው ለእግዚአብሔር ለአምላከ ጽድቅያላቸውን ፍቅርናክብር፤ ለሃይማኖታቸው ያላቸውን ጽናት፤ ለጨበጡት መስቀል ለመስዋዕትነት ምልክቱ ያላቸውን ስሜት ለአገራቸውና ለወገናቸውም ያላቸውን ታማኝነት አረጋገጡ። በመትረየስ ተደበደቡ። ዛሬ በዚህ ድርጊት ኢትዮጵያ ትኮራለች፤ ኢጣልያታፍራለች።
ጴጥሮሳዊነት የምለው የአቡነጴጥሮስን ዓይነት የእምቢተኛነት መንፈስ ነው። ጴጥሮሳዊነት በእግዚአብሔር አምላክ ጽድቅነት (ጽድቅ እውነት ማለት ነው) አምኖ የራስንም ኃላፊነት ከነውጤቱ የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው ብሎመቀበል ነው። ጴጥሮሳዊነት በመሠረቱ መንፈሳዊነት በመሆኑ የሚመካበት ኃይል መንፈሳዊ እንጂ አካላዊ ወይም ጠመንጃ አይደለም። የጴጥሮሳዊነትም ዓላማ አስፈላጊ ከሆ ነለእምነቱ ለመሞት እንጂ ለመግደል አይደለም። ሰው ሲገደል የሚቀረው በድንሬሣነው። ገዳዩም ከዚያ ከበድን ሬሣ የተለየ፤ ወይም ከተጠቀመበት የመግደያ መሣሪያ የማይለይ ነው። በአካል ደረጃ ገዳይና የተገዳዩ ሬሣ ቢመሳሰሉም፣ በመንፈስ ደረጃ የማይገናኙ ናቸው። እውነትን እገድላለሁ ብሎ የሰውን ሕይወት የሚያጠፋ በድን፣ እውነትና የሰው ደም እንዳስደነበረውና እንዳቃዠው ከበድንነት ወደ በድንነት ይተላለፋል። ለእውነት የተገደለው ግን እውነትን በሕይወቱ መስዋዕትነት አዳብሮና አፋፍቶ ያልፋል። መግደል የአእምሮ በሽተኞችና የልጆች ጨዋታ ነው። ለመሞት መዘጋጀትና ለእውነትና ለእምነት መሞት ግን ወኔን ይጠይቃል፤ መንፈሳዊወኔን።
የኢትዮጵያ ባህል ለጠመንጃ የሚሰጠው ክብር ከራሱ ከሰውነት ክብሩ ጋር የተያያዘ ነው። ጠመንጃ ኃይል ይሆናል፤ አያስጠቃም። ገዳይጀግና ተብሎ ይከበራል። ሠርቶ ከመክበር ያንድ መኳንንት ሎሌ ሆኖ ጠመንጃ መሸከም ያስከብር ነበር፤ አሁንም አልቀረም። ይህንን ክፉና የማይጠቅም ባህል በጴጥሮሳዊነት መለወጥ ያስፈልገናል። በጠመንጃ ኃይል ከመተማመን በመንፈሳችን ኃይል መተማመኑ ወደ ተሻለ የእድገት ጎዳና ያመራናል። ለጠመንጃ የማይበገር መንፈስ በመሀከላችን ሲዳብር ከጠመንጃ ይልቅ በጽሑፍ፤ ከጥይት ይልቅ በቃላት ቅራኔዎቻችንን ማለሳለሱ ወደ ሥልጣኔ ፈር ውስጥ ያስገባናል። እምነታችን የቱንም ያህል ቢለያይ፣ ሃሳባችን ቢራራቅና መግባባት የሚያስቸግር ቢሆንም ሃሳቦቻችን ይጋጩ፣ ይፋጩ እንጂ እኛ ጎራዴ መዝዘን ወይም ጠመንጃ አጉርሰን፣ ከአእምሮና ከመንፈስ ደረጃ ወደ እንሰሳነት ደረጃ ወርደን ስንጋደል እምነቶቻችንና አሳቦቻችን ያደፍጣሉ እንጂ እንደማይሞቱ ይግባን።
ጴጥሮሳዊነት በአቡነጴጥሮስ መስዋዕትነት ላይ የተመሠረተ የኢትዮጵያዊነት መንፈስ ነው። አቡነጴጥሮስ ኢትዮጵያዊ በመሆናቸው፣ የተሰውበትም ዋና ምክንያትየኢትዮጵያነፃነትበመሆኑጴጥሮሳዊነትንኢትዮጵያዊነትእንበለውእንጂዓለምከተፈጠረጀምሮየሰውልጆችታሪክበየአገሩየሚያሳየውየሰውመንፈስነው።ስለዚህምጴጥሮሳዊነትዓለምአቀፋዊነትባሕርይምአለው።
እውነትን ክዶ በውሸት ከመኖር ለእውነት ሞቶ እውነትን ሕያው ማድረግ የመንፈስ ዕርገት ነው። እንዲህ ዓይነቱ የመንፈስ ዕርገት የሚቀጥለውን ትውልድ ከእንሰሳት ደረጃ ወደላቀ የሰውነት ደረጃያነሣዋል። ከዚህ የተሻለ ውርስ አይኖርም። ጠመንጃ የያዘ ሁል ጊዜም እንዲያሸንፈን መንፈሳችን ከተዳ ከመለጠመንጃ መድኃኒቱ ጠመንጃን ማንሣት እየሆነ እስከዛሬ እንደነበረው ወደፊትም ይቀጥላል። ይህንን የቁልቁለት መንገድ በጴጥሮሳዊነትልና ቆመውና ወደዕርገት እንዲያመራን ማድረግ እንችላለን። የእያንዳንዳችንን ውሳኔ የሚጠይቅ ነው።
ኢትዮጵያዊነት ከየት ወዴት? ገጽ 42-43
ተጻፈ 1986 ..

taken from :    http://www.ethiopiazare.com/articles-55/opinion/2994-petrosawinet

No comments:

Post a Comment