Saturday, August 11, 2012

የፌዴራል ከፍተኛዉ ፍርድ ቤት በአንዱአለም አራጌና በእስክንድር ነጋ ላይ የተላለፈዉን የፍርደ ቤት ዉሳኔ አስመልቶ አንድነት ፓርቲ ያወጣዉን መግለጨ ህገ ወጥ ነዉ ሲል የፓርቲዉን ከፍተኛ ባለስልጣናት አስጠነቀቀ


አንድነት ፓርቲ በአንዱአለም አራጌ፤ በእስክንድር ነጋና በሌሎችም ተከሳሾች ላይ የፌፌራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ያሳለፈዉን ዉሳኔ በማዉገዙ ፍርድ ቤቱ የፓርቲዉን ከፍተኛ ባለስልጣናት አስጠርቶ ተግሳጽና ማስጠንቀቂያ እንደሰጠ ሁኔታዉን በቅርብ የተከታተለዉ የግንቦት ሰባት ድምጽ ዘጋቢ ገለጸ። የመለስ ዜናዊ አገዛዝ የፖለቲካ መሳሪያ የሆነዉ የፌዴራሉ ፍርድ ቤት “የፓርቲዉ መግለጫ የፍርድ ቤቱን ነፃነት የሚጋፋ ብቻ ሳይሆን አደጋ ላይ የሚጥል ነዉ” ብሎ ሲናገር ችሎቱ ዉስጥ የነበረዉን አብዛኛዉ ሰዉ እንደሳቀ ምንጫችን አክሎ ገልጿል። ሊገፋ ቀርቶ ለእይታም የሚበቃ ነፃነት የሌለዉና የወያኔ ስርአት እስረኛ የሆነዉ ፍርድ ቤት ስለ ነፃነት ማዉራቱ በአስተሳሰብ ደረጃ “አያ ጅቦ ሰታመካኝ ብላኝ” ካለችዉ እንስሳ ምንም እንደማይሻል በግልጽ ያሳያል ሲሉ የፍርድ ቤቱን ዉሎ በቅርብ የተከታተሉ ሁሉ በአጽንኦት ተናግረዋል።
የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የአንድነት ፓርቲ መሪዎችን ፍርድ ቤት አስጠርቶ ፓርቲዉ የፍርድ ቤቱን ዉሳኔ አስመልክቶ ያወጣዉ መግለጫ በከፍተኛ ደረጃ የሚያስቀጣ ጥፋት መሆኑን ከገለጸ በኋላ ፓርቲዉ ለመድበለ ፓርቲ ስርአት ግንባታ የሚያደርገዉን አስተቃጽኦ ከግምት ዉስጥ በማስገባት ይህንን ጥፋት በማስጠንቀቂያ እንደሚያልፈዉ ጨምሮ ገልጿል። የፓርቲዉ ከፍተኛ አመራር አባል በሆነዉ በአንዱአለም አራጌ ላይ የግፍ ፍርድ የፈረደዉ ፍርፍ ቤት አንድነት ፓርቲ ለመድበለ ፓርቲ ስርአት ግንባታ ስለሚያደርገዉ አስተዋጽኦ መናገሩ ኢትዮጵያ ዉስጥ የመድበለ ፓርቲ ስርአት ያለ ለማስመሰል የተነገረ ተራ የመንደር ወሬ ከመሆኑ ዉጭ ምንም ቁም ነገር ያላዘለ ባዶ አባባል መሆኑን አንዳንድ የስርአቱ ደጋፊዎች ጭምር በይፋ በመናገር ላይ ናቸዉ።
መለስ ዜናዊ ከኢትዮጵያ የፖለቲካ መድረክ ዳግም ላይመለስ ጠፍቷል እየተባለ በሚነገርበት ወቅት የወያኔ አባላት ምን ያክል ከመለስ ዜናዊ የከፉ ሊሆኑ እንደሚችሉ ለማሳየት ከግዜ ጋር እሽቅድምድም የገቡ ይመስላል ስትል አንዲት ችሎቱ ዉስት ቁጭ ብላ የፍርድ ቤቱን ዉሳኔ የተከታተለች የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የህግ ተማሪ ለግንቦት ሰባት ድምጽ ዘጋቢ በሰጠችዉ ቃለ ምልልስ ተናግራለች።የህግ ተማሪዋ ከዚህ ጋር በማያያዝ ይህ የወያኔዎች ድንብርብሩ የወጣ ሩጫ የሚያሳየን እነዚህ ዘረኞች ህዝባዊዉን ትግል ለመግታትና ብሎም ለማኮላሸት የማያደርጉት ነገር አንደሌለ ነዉ፡ ስለሆነም እኛ ኢትዮጵያዉያን በአጭር ታጥቀን ወያኔን በፍጥነት የማናስወግደዉ ከሆነ መጪዉ ግዜ ከቀድሞዉ የከፋ ሊሆን እንደሚችል ተናግራለች።

    No comments:

    Post a Comment