Saturday, August 11, 2012

አንጋፋዉ የህወሃት መሪና መስራች ስብሀት ነጋ ከጀርመን ድምጽ ሬዲዮ ጋር ባደረገዉ ቃለ ምልልስ “ባጠቃላይ ሲታይ አሁን ህግ መንግስቱን ተቀብለን ነዉ የምንሄደዉ፤ ያለነዉ በስልጣን ዝዉዉር አካባአቢ ነዉ ” በማለት የመለስ ዜናዊን መጨረሻ የሚጠቁም ነገር ተናገረ


ዘረኛዉ መለስ ዜናዊ ታምሞ የአልጋ ቁራኛ ከሆነበት ቀን ጀምሮ አንዴ አልታመመም፤ አንዴ ተሽሎታል በሌላ ግዜ ደግሞ እረፍት ላይ ነዉ እያሉ የባጥ የቆጡን ሲቀበጣጥሩ የከረሙት የወያኔ ባለስልጣኖች ከሰሞኑ በአንጋፋ መሪያቸዉ በስብሐት ነጋ በኩል አገራችን ኢትዮጵያ የስልጣን ዝዉዉር ላይ እንደምትገኝ በእጅ አዙር ተናግረዋል። ስብሐት ነጋ ባለፈዉ ማክሰኞ ለጀርመን ድምጽ ሬዲዮ በሰጠዉ ቃለምልልስ በረከት ስምኦንና ሽመልስ ከማል ሁለት ወር ሙሉ ሲደብቁ የከረሙትን የጠ/ሚኒስትሩን የስልጣን ሽግግር ጉዳይ ሳይወድ በግዱ ሽፍንፍን ባለ መልኩ ጠቁሞ አልፏል።
እገሌ ኖረም አልኖረ ወይም እገሊት ኖረች አልኖረች በህገመንግስቱ በሰፈረዉ መሠረት የአመራሩ አሰራር ይቀጥላል ሲል የነበረዉ ስብሀት ነጋ ይህንን ጠቋሚ ንግግር ያደረገዉ ከሰሞኑ የጀርመን ድምጽ ሬዲዮ -  የኢትዮጵያ ህግ መንግስት ምክትል ጠ/ሚኒስትሩ ያለዉን ስልጣን አያረጋግጥም በወኪልነት ለረጂም ግዜ መቆየት ደግሞ ችግር ያመጣልና እዚህ ላይ የእርስዎ አስተያየት ምን ይመስላል ተብሎ የተጠየቀዉን ጥያቄ ሲመልስ ነዉ።
ስብሀት ነጋ በዚህ ንግግሩ የስልጣን ሽግግሩን ብቻ ሳይሆን መለስ ዜናዊ ተሽሎት በቅርቡ ወደ መደበኛ ስራዉ ይመለሳል ሲል በረከት ስምኦን የሰጠዉን መግለጫ ዉድቅ ያደረገዉ ከመሆኑም በላይ መለስ ዜናዊ ሞቷል ተብሎ የተነገረዉ ዜና ይበልጥ ተቀባይነት እንዲያገኝ አድርጓል።
በሬዲዮ ቃለምልልሱ ወቅት ከዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳና ከፕሮፌሰር አድነዉ አዲስ ጋር አብሮ የቀረበዉ ስብሀት ነጋ የኢትዮጵያ ፓርላማ ጠ/ሚኒስትሩን መሾም ብቻ ሳይሆን ካሰኘዉ በየወሩ መቀያየርም ይችላል ሲል ከመደመጡም በላይ ለተጠየቀዉ ጥያቄ ትክክለኛ መልስ ከመስጠት ይልቅ ያንን የተለመደ ዘረኛ የፖለቲካ ጅራፉን እንዳጮኸ የሦስትዮሹ ዉይይት ተጠናቅቋል።
ስብሀት ነጋ ኢትዮጵያ ዉስጥ ዋናዉ የመሪነት ቦታ ለተቀሩት ሦስቱ የኢህአዴግ ድርጅቶች የሚዳረስበት ሁኔታ ይኖራል ወይስ ዋናዉ ቁንጮ መሪ ህወሀት ብቻ ነዉ የመሪነቱን ቦታ እንደያዘ የሚቀጥለዉ ብሎ ለጠየቀዉ ጥያቄ ሲመለስ ከጥያቄዉ ጋር ፍጹም የማይገናኝ መልስ በመስጠትና አንዳንዴም ጠያቂዉ ላይ “አባባልህ ልክ አይደለም” የሚል ክስ በመሰንዘር ኢትዮጵያ ዉስጥ ዋናዉ የመሪነት ቦታ ከህወሀት እጅ በፍጸም አንደማይወጣ ግልጽ አድርጓል።

No comments:

Post a Comment