Saturday, August 4, 2012

የቤት ሥራችን (በወ/ሪት ዙፋን አማረ)

ወሪት ዙፋን አማረ

የስሞኑ አበይት ዜና የሆነው የአቶ መለስ በሕይወት የመኖርና ያለ መኖር ጥያቄ በሁላችንም ዘንድ ትኩረትን የሳበ ዜና መሆኑ ተገቢ ነው::
መለስ ለአለፉት ሁለት አስርተ ዓመታት የስልጣን ዘመኑ የኢትዮጵያን ሕዝብ በጐሳ፣ በሃይማኖትና በመሳሰሉ ልዩነቶች ለመከፋፈልና ኢትዮጵያን ለመበታተን ጥረት ያደረገ፣  ኢትዮጵያውያን በሀገራችንም ሆነ ከሀገራችን ውጭ አንገታችንን እንድንደፋ፣ ለድሕነት ፣ለስደት፣ለእስር፣ለእንግልት
እንድንዳረግ ከፍተኛውን ሚና የተጫወተ በዜግነታችን ብቻ ሊኖረን የሚገባን መብት በአዋጅ የነፈገ በሀገራችን ሁለተኛ ዜጋ ሆኖ የመኖር መራራ ጽዋን በግድ እንድንጐነጭ ያደረገ በመሆኑ የዚህ የሀገር ነቀርሳ በአንድም ሆነ በሌላ መልኩ መነቀል ዜና ካላሳሰበን ሌላ ምንም የሚያሳስበን አንገብጋቢ ጉዳይ
አይኖርም::

መለስ በሕዋሃትም ሆነ በኢትዮጵያ ያለው የሰልጣን እርከን ለ 57 ዓመት እንደ አላማ ላራመደው ኢትዮጵያን የማፈራረስ ሕልም አመች ሁኔታን የፈጠረለት በመሆኑ ለእኛ ለሀገራችን በጐ ለምንመኝ የሀገራችን ሰላም ማደር ለሚያሳስበን የጐን ውጋት በመሆኑ የእስትንፋሱ ቀጥ ማለት እንደ ሰብዓዊ ፍጡር የሚያሳዝነን ቢሆንም ሀገርን ከመታደግ አኳያ ጮቤ የሚያስረግጥ ነው ለምን ቢባል መለስ በውስጡ የፈጠረው ኢትዮጵያን እንደ ሀገርና ኢትዮጵያውያንን እንደ ሕዝብ የመጥላትና የመበቀል አባዜ አብሮት ስለሚቀበር ነዉ ኢትዮጵያን ለመጥላቱ ሌላ መረጃ አያስፈልገኝም በስልጣን ዘመኑ ያደረጋቸው ንግግሮቹ ዋቢ ስለሚሆኑኝ::

መለስ እቅዱና ዓላማው ሳይሳካለት በአጭር መቀጨቱ ጮቤ የሚያስረግጠን ወደፊት እንመሰርታታለን ለምንላት ፍትሕ ፣እኩልነትና የሕዝቦች መብት የሚከበርባት ዜጐች በማንነታቸው ኮርተው  የሚኖሩባት ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ የጀመርነውን መንገድ ስለሚያቀልልን ነው ይህንን ስላችሁ ደግሞ መንገዳችን ከአሁን በኋላ አልጋ በአልጋ ነው ለማለት አይደለም በሱአምሳል የተፈጠሩ ጥቂት የሀገር መዝገሮችን የመንቀል ሀላፊነት አሁንም ይጠብቀናል::

የመለስ መወገድ ብቻ በራሱ  ለሀገራችን መብትሄ እንደማያመጣ እሙን ነው ለውጥ የሚያመጣው
በትግሉ ውስጥ የምንፈጥረው የሀይል ሚዛን መሆኑ ለማንም የተሰወረ አይደለም ስለሆነም ይህንን
የሀይል ሚዛን እንዴት እንፍጠር የሚለው የሁላችንም የቤት ሥራ መሆን ይኖርበታል የሚል እምነት
አለኝ ለወያኔ የመተንፈሻ ጊዜ መስጠት አያስፈልግም የሀይል ሚዛኑን ለመፍጠር በግለሰብም ደረጃ
ይሁን በቡድን የሚደረግን ትግል በአንድ የጋራ መስመር ማሰባሰብ ግድ የሚለን የወቅቱ ጥያቄ ነው
ስለሆነም ሁላችንም የቤት ሥራችንን ለመወጣት የበኩላችንን እናድርግ::

እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ያስባት !

No comments:

Post a Comment