Saturday, October 13, 2012

ሟቹ ጠቅላይ ሚንስትር ለኤርትራ ተቃዋሚዎች ባህር ዳር ላይ የጀምረውት የነበረው የሬዲዮ ጣቢያ ግንባታ ተቋረጠ


መለስ ዜናዊ ስልጣን ላይ በቆየባቸዉ አመታት ያከናውናቸው የነበሩት በርካታ ጉዳዮችን ለፓርቲውም ሆነ ለሚንስትሮች ምክር ቤትም ወይም ለይስሙላ ፓርላማ እንደማያሳውቅ ምንጮች አጋለጡ
ኢትዮጵያ አገራችንን ለ21 አመታት የገዛው ዘረኛውና አምባገነኑ መለስ ዜናዊ ከፍተኛ በጀት የሚጠይቁ ትላልቅ ውሳኔዎችን በዙሪያው ላሰባሰባቸው የካቢኔ ምንስትሮችም ሆነ ለፓርላማው ሳያሳውቅ በራሱ ፈቃድ ብቻ ያስተላልፍና ያስፈጽም እንደነበረ ጉዳዩን በቅርበት ይከታተሉ ከነበሩ ሚንስተሮች የተገኘ መረጃ አጋለጠ።
መለስ ዜናዊ በህይወት በነበረበት ወቅት ለማንም ሳያማክር በግል ሥልጣኑ አስጀምሮት ከነበሩ ፕሮጄክቶች አንዱ ለኤርትራ ተቃዋሚዎች ይሰጥ የነበረው የፋይናንስና የማቴሪያል እርዳታ እንደነበረ የገለጹ ምንጮች የርሱን መሞት ተከትሎ ተቃዋሚዎቹ ከፍተኛ ችግር እንደገጠማቸው ገልጸዋል።
የኤርትራን ተቃዋሚዎች ለማደራጀት መለስ ዜናዊ በግሉ ይዞት በነበረው ፕሮጄክት ባህር ዳር ከተማ ዉስጥ ተቃዋሚዎቹ ወደ ኤርትራ የሚያስተላለፉት የሬዲዮ ስርጭት በጥራት እንዲሰማ ከፍተኛ ገንዘብ በመመደብ የሬዲዮ ጣቢያ ግንባታ ስራ ከተጀመረ ቦኋላ ከዚህ አለም በሞት በመለየቱ ምክንያት የፕሮጀክቱ ባለቤቶች የሆኑት የኤርትራ መንግስት ተቃዋሚ ኃይሎች ግንባታው እንዲጠናቀቅላቸው ለመጠየቅ ከመለስ ዜናዊ ጋር በነበራቸው ቅርበት ስለፕሮጀክቱ ሊያውቁ ይችላሉ የተባሉትን የፍትህ ምንስትሩ ብርሃን ሃይሉን፤ የቀድሞ የአማራ ክልል ምክትል ፕሬዝዳንትና የአሁኑ ምክትል ጠቅላይ ምንስቴርን ድመቀ መኮንንን፤ የአማራ ክልል ፕሬዝዳንት አያለው ጎበዜን በየተራ ቢያነጋግሩም ጉዳዩን አውቃለሁ የሚል አንድም ባለሥልጣን እንዳልተገኘ የደረሰን መረጃ አጋልጦአል።ከሁሉም የሚገርመው ስለጉዳዩ ያውቃሉ ተብለው ከተጠየቁት መካከል ምክትል ጠቅላይ ምንስትር ሆኖ የተሾመው የትምህርት ሚኒስትሩ ደመቀ መኮንን ጭራሹን የኤርትራ ተቃዋሚ አዲስ አበባ ዉስጥ መኖሩንም ሰምቶ እንደማያዉቅ በመናገር እርዳታ ፈላጊዎቹን አስደንግጦአል።በቅርቡ ጠ/ሚኒስትር ሆኖ የተሾመዉ ኃ/ማሪያም ደሳለኝ ፓርቲዉ ኢህአዴግ የረጂም ግዜ የጋራ አመራር ልምድ አለዉ ብሎ ሲናገር የተደመጠ ቢሆንም እሱ እራሱ የአገሪቱ ምክትል ጠ/ሚኒስትር ሆኖ በቆየባቸዉ ሁለት አመታት ዉስጥ ዉሳኔያቸዉንም ሆነ አፈጻጸማቸዉን በፍጹም የማያዉቃቸዉን አያሌ ዉሳኔዎች መለስ ዜናዊ ብቻዉን ይወስን እንደነበር እነዚሁ ዉስጥ አዋቂ ምንጮች ገልጸዉ እንደዚህ አይነት ሀላፊነት የጎደላቸዉና አገርን ለችግር የሚያጋልጡ የመለስ ዜናዊ ስራዎች ከአሁን በኋላ በስፋት ለህዝብ ይፋ ሊሆኑ አንደሚችሉ ጠቁመዋል።
source:  http://www.maledatimes.com/category/news/

No comments:

Post a Comment