Sunday, November 25, 2012

”መፈረካከሱ ቀጥሏል፤ ፍርሃት፣ ጭንቀትና መደነባበሩም በወያኔ መንደር ተባብሷል”


የሐምሌና ነሐሴ ከባድ ዝናባማ ወራት ጠቅልለው ከሄዱ ቆይተዋል። ለወጥሮው የኢትዮጵያን ሰማይ ሸፍኖ የነበረው ከባድ ጥቁር ዳመና ከረር ከረር እያለች በመጣችው የፀሐይ ሙቀት ምክንያት እየተሸነፈ እንደ ባለሙያ ሴት የጥጥ ንድፍ እዚህም እዚያም በተን በተን ያለ እጅግ በጣም ስስ ጉም መሆን ከጀመረ ውሎ አድሯል። ሜዳ፣ ጋራና ሸንተረሩ ውሃ ጠግቦ በቃኝ ብሎ በሙሉ ደረቱ የሚያፈስባቸውና በተለምዶ የአበባ ወራት ተብለው የሚጠሩት ወራቶችም ምድሪቱን ካስወቡበት ምትሃታማ አስደማሚና ህሊናን ያዥ ህብር ቀለማቸው እየሸሹ የምድሪቱን አላባ እንካችሁ የሚሉበት ወርሃ ጥጋብ ወርሃ ምርት ጊዜ እየደረሰ ነው። ጓዳ ጎድጋዳው፣ ሸጥና ወንዙ፣ ኩሬ ሸለቆው፣ ወጣ ገባ ተራራው ባጠቃላይ ምድሪቱ በሚላስ በሚቀመስ ሲሳይ የምትጎበኝበትና የምትሞላበት መልካም የደስታና የጥጋብ ወራት፤ ወርሃ ምርት ኢትዮጵያ።
የእያንዳንዱ አርሶ አደር ጎጆ በአንጻራዊ ሲሳይና ደስታ በሚጎበኝበት በዚህ ጊዜ፤ ምድሪቱ ያላትን በረከት ያለስስት እየጋበዘች ባለችበት በዚህ ወራት፤ የምግብ እጦት ፍርሃት ለጊዜውም ቢሆን በተረሳበት፣ የርሃብና የስደት ፍርሃት ላፍታ እንኳ በማይታሰብበት የጥጋብ ወራት፣ ምርት እንዴት እንደሚሰበሰብ እንጅ የጥላቻ፣ የመራራቅና የጦርነት ስጋት እንደደራሽ እንግዳ እንኳ ቢሆን ትዝ በማይልበት በዚህ የኢትዮጵያ የደስታና የሃሴት ወራት ምነው ወያኔ ፍርሃት ፍርሃት አለውሳ። በ99.6 የኢትዮጵያ ህዝብ ተመረጥኩ እያለ ያወራበት አፉ ሳይደርቅ እንዴት ወያኔ በህዝባችን የልበ ሙሉነት ወራት ስለፍርሃት ያወራል? ምነው ወያኔዎች ተራሮችን ያንቀጠቀጡ ጀግኖች አልነበሩም እንዴ? ታዲያ ሰሞኑን ምን ተገኝቶ ነው ተንዘፈዘፉሳ።
አርበኞች ግንባር በየቀኑ ፋታ አሳጥቶ እየኮረኮመኝ ነው፤ የትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ትህዴን) ደግሞ ያለ እረፍት እየቆነጠጠኝ ነው፤ ፌደራል ፖሊስም በተከታታይ የእከዳና ወደ ጠላት እየተቀላቀለ ነው፤ በጠላት ተከበናል፤ ስለ ኢትዮጵያ እንደሚያስብ ጥሩ መንግስትና ለሕዝብ እንደሚጨነቅ አመራርም ሀገራችንን ለማፍረስ ተነስተውብናል ዘምተን ልንከላከላቸው ይገባል ወዘተ ወዘተ እና ሌሎችም። የወያኔ የትንፋሽ እርግብግቢት ፍርሃቱን እያሳበቀበት ነው፤ በእርግጥም ወያኔ መፈረካከስ ጀምሯል። ሰራዊቱን ይቅርታ ፌደራል ፖሊስን ወደ ግዳጅ ለመላክ የተጠቀሙበት የማሳመኛ ዘዴ እንኳ እርስ በርሱ የሚጋጭና የራስ መተማመን የጎደለው ደካማ ነበር። እንድ ጊዜ ”ኢትዮጵያ ሀገሬ ማለትና ስለ አድዋ ማውራት ዋጋ የለውም ታሪከ ስለሆነ” ሲሉ በሌላ በኩል ደግሞ ”ሰራዊታችን ግዳጅን በመፈጸም ያታወቃል ጀግና ነው ለዚህም ታሪክ ምስክር ነው” ይሉናል። ባንድ ራስ ሁለት ምላስ ይላል ይህን ነው።
ያርበኞች ግንባር፣ ትህዴን እና ሌሎችም የዴሞክራሲ ሃይሎች ለሀገራችን ሉአላዊነትና ለሕዝባችን አርነት ከወያኔ ጋር ወያኔ በመረጠው ቋንቋ ግንባር ለግንባር ሲፋለሙ ይህ የመጀመሪያቸው አይደለም የመጨረሻቸውም አይሆንም። ወያኔ ተጨነቀም አለቀሰ፣ ፈራም ተርበደበደ፣ አቅራራም አስጠነቀቀ ሀገራችን ከወያኔ ነጻ አስክትሆንና ሕዝባችንም በነፃነት መንቀሳቀስ እስከሚችል ድረስ ከዲሞክራሲያዊ ሃያሎች የሚደርስበት ጥቃት ተጠናክሮ ይቀጥላል። ስለዚህም የነዚህ ዴሞክራሲያዊ ሃይሎች ጥቃት ላሁኑ የወያኔ ባለስልጣናት ለቅሶና ሙሾ ሰበብ ይሆን እንደሁ እንጅ እንደዋና ምክንያት ሊጠቀስ አይችልም።
ስለሆነም የወያኔ ባለስልጣናት ፍርሃትና ጭንቀት ዋናው መነሻ የሰራዊቱና ፌደራል ፖሊስ በገፍ መኮብለልና ከዴሞክራሲያዊ ሃይሎች ጋር መቀለቀል ነው እንጅ ሌሎች ምክንያቶች ሁሉ አጃቢዎች ናቸው።
ወያኔ በጣም ከመረበሹና ግራ ከመጋባቱ የተነሳ ፌደራል ፖሊስን እንደ ሀገሪቱ ጦር ሰራዊት በየጦር ግንባሩ በግልጽ ወታደራዊ ትእዛዝ እያዘመተ ይገኛል። ይህም ፌደራል ፖሊስ ከተመሰረተበትና ከሰለጠነበት ዓላማ ውጭ እንዲያገለግል እየተገደደ መሆኑን ያሳያል። ይህን በማድረግም ወያኔ ከስልጠናው ዓላማ ውጭ በማንአለብኝነት ፖሊስን ወደ ግንባር በማዝመት የራሱ የወያኔ ህገመንግስት ያጸደቀውን የጋራ ስምምነት እንኳ በመጣስ አምባገነንነቱን መግልጽ አሳይቷል። በግልባጩ የወያኔ ድንጉጥ ባለስልጣናት ግን በቅድሚያ እራሳቸው የደፈጠጡትን ተራራ የሚያክል የህግ ሽረት ትተው ከድተው ከዴሞክራሲያዊ ሃይሎች ጋር ስለተቀላቀሉት ፌደራል ፖሊሶች ውል ማፍረስ እየተርበተበቱና እየተንተባተቡም ቢሆን ያለ ሃፍረት ሊገልጹ ሲሞክሩ ያታያሉ።
የወያኔ ፌደራል ፖሊስ ድረ ገጽ በግልጽ እንደሚያሳው የፌደራል ፖሊስ ራዕይ ዓለም አቀፍ ደረጃን የጠበቀ ፤ የህዝቦችን
ህጐችን በማክበርና በማስከበር ሕብረተሰቡን በወንጀል መከላከልና ምርመራ በማሳተፍ የመንግስትና የሕዝብን ሠላምና ደህንነት መጠበቅና ማረጋገጥ ነው ይላል፡፡ ስለሆነም ከላይ እንዳየነው ወያኔ ራሱ ካስቀመጠው ብንነሳ እንኳ ፌደራል ፖሊስ ከሕዝብ ጋር ሆኖ ሕዝብን ያገለግላል እንጅ እንዲህ ሰሞኑን እንደሰማነውና እንዳየነው የወያኔ ባለስልጣናት ወዬው እናቴ አይነት ልቅሶ እና ራስ መተማመን የጎደለው ልፍስፍስ ትእዛዝ እንደ ሀገር ጥበቃ ሰራዊት ታጥቆና ወታደራዊ ትእዛዝ እየተቀበለ ድንበር ለማስከበር እንዲዘምት የሚገደድ አልነበረም። አይደለምም።
ስለዚህ የሀገራችን ዴሞክራሲያዊ ሃይሎችና አባላት እንዲሁም ሰፊው የኢትዮጵያ ሕዝብ የወያኔ ጀምበር እየተለቀች መሆኑን ከዚህ ማሳያ በላይ ሌሎች ማረጋገጫዎች አያሹንም። ወያኔ ከመዳከምም አልፎ በያቅጣጫው እየተፈረካከሰና እየተለያዬ በራሱ ለመጥፋት ተቃርቧል። ስለሆነም ከወያኔ በሗላ ስለሚመጣው መንግስት መነጋገርና መወያየት ከማስፈለጉም በላይ ይህን ጉዳይ ለማስፈጸም እንድ ሆኖ መቆምና እየሞተ ያለውን ወያኔ ግብአተ መሬት ማፋተን ይጠበቅብናል።
“ድር ቢያብር አንበሳ ያስር” ነውና ብሂሉ ይነስም ይብዛ የሚናቅ እገዛ የለም። ዴሞክራሲያዊ ሃይሎችን የሚያጠናክር፣ የሕዝበችንን ሞራል የሚገነባና ወደ አንድ አቅጣጫ የሚያመጣ፣ ጠላት ወያኔን የሚያጋልጥ ማንኛውም አይነት መረጃ በማቅረብ፣ ተስማሚውን ወቅት፣ ሁኔታና ጊዜ በመምረጥ ወያኔን በመክዳት ከዲሞክራሲያዊ ሃይሎች ጋር በመቀላቀል ወያኔን በማደከም ትግላችንን ማስፋትና ማጠናከር ይቻላል። ለዚህ ደግሞ ቀጠሮ አያስፈልገንም ዛሬውኑ ወስነን ስራችንን እንጀምር።
እርካታና አመኔታ ያረጋገጠ የፖሊስ አገልግሎት ተፈጥሮ ማየት የሚል ሲሆን፡፡
ዓላማውም የሀገሪቱንሕገ-መንግስትናሌሎ

No comments:

Post a Comment